top of page

ነሐሴ 21፣2016 - ላለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 27, 2024
  • 2 min read

ላለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍጫቻ ቋንቋ ብቻ ሲማሩ የነበረ ቢሆንም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡


በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ባሉ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡


በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ህፃናት ወይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡


አሁን ግን በመጭው የትምህርት ዘመን ህፃናት ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡


ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ኛውን ጉባኤ ላይ ነው።



በጉባኤውም የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የዘርፉ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።


ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ እናደርጋለን ያሉት ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር) ተማሪዎቹ የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ሲል የሚማሯቸው ትምህርቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስለሚሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ቋንቋውን እንዲያውቁት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡


አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ከገባት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲማሩ የቆዩት በአፍመፍቻ ቋንቋቸው ሆኖ ሳለ በመጭው የትምህርት ዘመን የእንግሊዘኛ ቋንቋ መካተት ያስፈለገበትን ምክንያት የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ይህንን ይላሉ፡፡


የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ደኛ ጉባኤ ላይ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጋጥመውኛል ያላቸውን ችግሮች አንስቷል።


በዚህም አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘውን መፀሀፍ የግል ትምህርት ቤቶች አለመጠቀማቸው፣ የ2ተኛ ደረጃ መፀሀፍት ህትመት በተማሪ ቁጥር ልክ ከትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ አለመምጣት ካጋጠሙ ችግሮች መካከል እንደሆኑ የሚናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ናቸው።


የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው 31ኛው የትምህርት ጉባኤ ''የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለአገር ብልጽግና'' በሚል መሪ ኃሳብ ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችና የ2017 ዕቅዶች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page