top of page

ታህሳስ 18፣2016 - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለሁሉም ችግር መንስኤ የሆነዉን የሰላም እጦት መፍታት ያስፈልጋል ማለታቸዉ ተሰማ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለሁሉም ችግር መንስኤ የሆነዉን የሰላም እጦት መፍታት ያስፈልጋል ማለታቸዉ ተሰማ፡፡

 

አፈጉባኤዉ ይህን የተናገሩት የምክር ቤቱን አስራ ሦስት ቋሚ ኮሚቴዎች የሁለት ወር አፈጻጸም ከአስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በመሆን በገመገሙበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከሕዝቡ የሚነሱ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎቹም ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ቅድሚያ ለሠላም ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

 

ለዚህም ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው የብሔራዊ ምክክር መድረክ ቶሎ ወደ ስራ እንዲገባ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይበጃል ማለታቸዉን ከምክርቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

 



በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባበዎች ያሉ ግጭቶች በሰዉ ሕይወት፣ በንብረት እና በሀገር ላይ የከፋ ቀዉስ እየስከተሉ እንዳሉ ኢሰመኮን ጭምሮ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

 

የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴም እያስተጓጎሉ ያሉት ግጭቶች እንዲቆሙ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ችግሩ ከመፈታት ይልቅ እየከፋ መምጣቱ ይነገራል፡፡

 

በአማራ፣ በሚበዛዉ ኦሮሚያ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  እና በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ይብዛም ይነስም ግጭት መኖሩን የሰላም ሚኒሰቴር  ይናገራል፡፡

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ በበኩላቸው በእጭር ጊዜ በርካታ ያሏችዉ  ስራዎች ተከናዉነዋል ያሉ ሲሆን በክትትልና ቁጥጥር ስራ የመጡትን ለውጦች በመገምገም ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲኖር ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

 

የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ለሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል ተብሏል፡፡

በቀጣይ በሚደረጉ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መንግስት በከፍተኛ ወጪ ያስገባው ማዳበሪያ ለተጠቃሚዎች  በአግባቡ መድረሱን ማየት  ያስፈልጋል ማለታቸዉ  ተስምቷል፡፡ 

 

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በክትትልና ቁጥጥር ስራቸው እያንዳንዱ ተቋም ሰላምን በሚመለከት ሀገራዊ አስተሳሰብን መገንባት ላይ ምን እየሰራ ነው የሚለውን ማየት እንደሚገባ አንስተዋል ተብሏል፡፡ 

 

በተጨማሪም በወይይቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንደ መንገድ፣ መብራት እና ውሃ ላይ እንዲሁም ከማህበራዊ ልማተ አኳያ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰራባቸው ይገባል መባሉን ተነግሯል፡፡

 

 

ያሬድ እንዳሻው

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page