top of page

'ቪዛ ካርድ' በኢትዮጵያ ጀማሪ ፊንቴኮችን አወዳድሮ ሽልማት ሊሰጥ መሆኑን ተናገረ


በአለም ላይ የካርድ ባንኪንግ ከሚሰጡ ቀዳሚ ፊንቴኮች መካከል አንዱ የሆነው VISA ካርድ በኢትዮጵያ ጀማሪ ፊንቴኮችን አወዳድሮ ሽልማት ሊሰጥ መሆኑን ተናገረ፡፡


ከተመሰረተ 60 ዓመት የሞላው VISA ከሶስት ዓመት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ መስራት መጀመሩ ይታወሳል፡፡


ቪዛ የፋይናንስ እና የባንክ አገልግሎትን አጣምረው የግብይት ሥርዓቱን የሚቀላጥፉ ፊንቴኮችን አወዳድሮ የሚሸልመው ‘’ቪዛ ኤቭሪዌር ኢኒሼቲቭ / Visa Everywhere Initiative’’ ሲል በጠራው ፕሮግራም አማካይነት መሆኑንን ሰምተናል፡፡


የቪዛ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ያሬድ እንዳለ ለሸገር እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ለሚካሄደው ውድድር 170 ፊንቴኮች መሳተፋቸውን፣ ከእዚህም ውስጥ አምስቱ መለየታቸውን አስረድተዋል፡፡


አምስቱ የመጨረሻዎቹ እጩዎች ካቻ፣ ላኪፔይ፣ ቀና፣ ስማይል ፔይ እና መርካቶ ፋይናንስ መሆናቸው ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page