top of page

ሰኔ 4፣ 2016 - የፀደቀው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ፀደቀ፡፡


የፀደቀው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡


የሰማዕታትን ቀን (የካቲት 12) እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን (ህዳር 29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ ታስበው መዋላቸው ይቀጥላሉ፡፡


ምክር ቤቱ #የህዝብ_በዓላትና የበዓላትን አከባበር መወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቀ ዓላማ ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የሴቶች ቀንና ሌሎችም በዓላት ታስበው የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡


አንድ የምክር ቤት አባል፤ #የብሔር_ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉ በአላት ውስጥ ለምን አልተካተተም ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበርና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡


አዋጁ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ አለባቸው ያላቸውን ተቋማትን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡


በዚህም የእለት ከእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች የጤና ተቋማትና መድሃኒት ቤቶች ለሕዝብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ተቋማት የእሳት አደጋ፣ መከላከል አገልግሎትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዳጅ ማደያዎች ክፍት ሆነው እንዲውሉ በአዋጁ ተቀምጠዋል፡፡


ዛሬ የፀደቀው አዋጅ የዘመን መለወጫ በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት እንዲከበርም ያዛል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page