top of page

ሰኔ 4፣ 2016 - የመጪው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 971.2 ቢሊየን ብር ሆኖ ለፓርላማው ቀረበ

የመጪው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 971.2 ቢሊየን ብር ሆኖ ለፓርላማው ቀረበ፡፡

 

ይህም ከ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡

 

ከዚህ የወጪ በጀት ውስጥ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት፣ 283 .2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲሁም 236.7 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍሆኖ መደልደሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

 

ለክልሎች ከተመደበው በጀት ውስጥ 14 ቢሊየን ብር የሚሆነው የዘላቂ ልማቶችን ለማስፈፀም ለክልሎች የተመደበ ድጋፍ እንደሆነ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡

 

ከቀረበው የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ ከፍተኛውን በጀት፤ ለመደበኛው የተያዘው በጀት እንደሆነ የተናገሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህም የጠቅላላውን በጀት 46.5 በመቶ ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡

 

ሰኔ 30 ከሚጠናቀቀው ከ2016 በጀት ዓመት ጋርም ሲመሳከር የ21.9 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

 

ከመደበኛ በጀት ውስጥ 128.2 ቢሊየን ብር ወይንም 28.2 በመቶ ለመደወዝ፣ ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያ ሲሆን 321.4 ቢሊየን ወይም 71.8 በመቶ ለስራ ማስኬጃ ተደግፎ የቀረበ መሆኑን አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page