top of page

ህዳር 26፣2017 - የህዳሴ ግድብ 4 ተርባይኖች 1,550 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጩ መሆኑን ተነገረ

የህዳሴ ግድብ 4 ተርባይኖች 1,550 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጩ መሆኑን ግድቡ ማስባበሪያ ፕሮጄክት ጽ/ቤት ተናገረ፡፡


ጽህፈት ቤቱ ለሸገር ራዲዮ በላከው መግለጫ እስካሁን ኃይል እያመነጩ ካሉት የግድቡ አራት ተርባይኖች ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው በሙሉ አቅማቸው 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖራቸው ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ 400 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው ብሏል፡፡


ከግድቡ በጥቅሉ በአሁኑ ወቅት 1,550 ሜጋ ዋት ሃይል እየተገኘ መሆኑንም ተናግሯል፡፡


የቀሪዎቹ 9 ዩኒቶች ተከላና የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሙከራ ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው ኃይል ማምረት ሲጀምሩ አሁን እንደሃገር ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በ83 በመቶ እንደሚያሳድገው በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 97.6 በመቶ እንደደረሰ የተናገረው የፅህፈት ቤቱ መግለጫ የኮርቻ ግድቡ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የግድቡን ቀኝ እና ግራ ክፍል የሚያገናኘው ድልድይ እየተጠናቀቀ ይገኛል ይላል፡፡

በተጨማሪም የማስተንፈሻ በሮቹም እንዲሁ ሙሉ በሙሉ ግንባታቸው ተጠናቅቋል፡፡


1,800 ሜትር የሚረዝመው እና ከባህር ጠለል በላይ 645 ሜትር ከፍታ ያለው የዋናው ግድብ የሲቪል ስራ 99. 6 በመቶ ላይ ደርሷል፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችም 87 በመቶ ላይ ናቸው ብሏል፡፡


የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅም አሁን እየተመረተ ያለውን 1,550 ሜጋ ዋት ጨምሮ ቀሪ 3,600 ሜጋ ዋት ታክሎበት ፕሮጀክት በአጠቃላይ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭና ሃገር አቀፍ ዓመታዊ የኃይል ምርቱን 83 በመቶ እንደሚያደርሰው ተናግሯል፡፡


በተያዘው የበጀት ዓመት አራት ወራት ለግድቡ ግንባታ ከ311 ሚሊዮን ብር በላይ ከህዝብ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ደግሞ ከ20.2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ማስባበሪያ ፕሮጄክት ጽ/ቤት ከላከልን መግለጫ ተመልክተናል።


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page