ወግ

ታህሳስ 21፣ 2012/ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህግ ውጪ የተገነቡ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደምወስድ እወቁት ብሏል

በከተማዋ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ህገ-ወጥ የቤት ግንባታዎችን እየለየ መሆኑንም አስተዳደሩ በፌስቡክ ገጹ ላይ ፅፎት ተመልክተናል፡፡እርምጃውን ጥር 2፣ 2012 እንደሚጀምርም በመረጃው ጠቅሷል፡፡በከተማዋ ባሉ 116 ወረዳዎች እወስደዋለሁ ባለው እርምጃ የአዲስ አበባ፣ የፌደራልና የኦሮሚያ ፖሊሶች እንዲሁም የከተማዋ አጎራባች ወረዳዎች ይሳተፋሉ ብሏል፡፡

ይህ እርምጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል እንደሚያስችለውም የከተማ አስተዳደሩ ጠቅሶታል፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ክፍት ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ እየታጠሩ ነው ያለው አስተዳደሩ ከላስቲክ ቤቶች ጀምሮ የተለያዩ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
ምላሽ

ታህሳስ 21፣ 2012/ በተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ ሙሉ በሙሉ ከታክስ ነፃ የተደረጉና ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠበቁ ምርቶች መኖራቸው ተነገረ

ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ 80 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይከፈልበት የነበረው የልብስ ማጠቢያ ማሽን በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆን ተደርጓል ተብሏል፡፡ይህም ዘመናዊ ኑሮን ለማበረታታትና የሴቶችን ድካም ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ መሆኑን በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተሩ አቶ ሙላይ ወልዱ ተናግረዋል፡፡በቀደመው አዋጅ 30 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይከፈልበት የነበረው የመመገቢያ ሰሃን ማጠቢያ ማሽንም በተመሳሳይ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ተደርጓል፡፡
ምላሽ

ታህሳስ 21፣ 2012/ አባይ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የዲጂታል ክፍያ መላዎችን ጀመርኩ አለ

ባንኩ ከአየር መንገዱ ጋር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መላዎችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተፈራርሟል፡፡ለዚሁ መላ የባንኩ ደንቦች በኦንላይን ባንኪንግ በመጠቀም ትኬት መቁረጥ ይችላሉ፡፡ሌሎችም አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ መባሉን ሰምተናል፡፡

አባይ ባንክ አገልግሎቱን በጀመረ በአንድ ሳምንት ውስጥ 1 ሚሊየን ገደማ ጥሪት መንቀሳቀሱን የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡በተያያዘም፣ ይህንኑ አገልግሎት ከአማርኛ በተጨማሪ በሁለት የአገር ቤት ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡የባንኩ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች 125 000 የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥርም 700 000 እንደደረሰ ሰምተናል፡፡

ተህቦ ንጉሤ
ምላሽ

ጥቅምት 5፣ 2012/ ኢትዮጵያ በምትከተለው ኋላ ቀር የግብርና ሥርዓት እና የግብርና ምርቶችን በአግባቡ ባለመጠቀሟ በአመት በሚሊዮኖች የሚቆጠር የምግብ ብክነት ይገጥማታል ተባለ

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የምግብ ቀን አስመልክቶ በኔዘርላንድስ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትና በአግሮፕሮፎክስ በተሰናዳው ፕሮግራም ላይ ተገኝተን እንደሰማነው ኢትዮጵያ ካላት የተመቸ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ አንፃር የግብርናን ስራ ያልተጠቀመችበት አገር ነች ተብሏል፡፡አገሪቱ ከምታመርታቸው የምግብ ምርቶች ውስጥም በአመት በአግባቡ ባለመሰብሰብ፣ በመጓጓዣ ችግር እንዲሁም በንግድ ሰንሰለት ውስጥ በሚፈጠር እክል ከ10 ሚሊየን ቶን በላይ የምግብ ምርት ይባክናል ተብሏል፡፡
ምላሽ

ጥቅምት 5፣2012/ ከመጪው ታህሳስ ወር ጀምሮ በኤሌክትሪክ ፍጆታ ላይ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ

ጭማሪው ለ4 ተከታታይ አመታት ተግባራዊ የሚደረገውና ባለፈው አመት የተጀመረው የታሪፍ ማሻሻያ አካል ነው ተብሏል፡፡ሁለተኛው ምዕራፍ የታሪፍ ጭማሪ ከፍተኛ የሀይል ተጠቃሚ በሆኑ ደንበኞች ላይ ጫና እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡ይህን የሰማነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀሙንና የ2012 እቅዱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ተገኝተን ነው፡፡ዝቅተኛ ሀይል የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ሀይል በመቆጠብ የታሪፍ ጭማሪው ሊያመጣባቸው ከሚችለው ጫና ነፃ መሆን እንደሚችሉ በመግለጫው ተነግሯል፡፡
ምላሽ
ወሬ መለያዎች
Reset filters
2021-06-19
ኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመታት በፊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የነበረው የሃገሪቱ አውድ አላላውስ አለን ፤  መስራት አልቻልንም…
2021-06-19
የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 በሚካሄደው ምርጫ አዲስ አበቤዎች ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተወካዮቻቸው 23 እጩዎችን ይመርጣሉ…
2021-06-19
ሕዝብ ያሻውን እንዲመርጥ ዴሞክራሲያዊ  መብቱን  እንዲጠቀም  የመራጮች ትምህርት መስጠት አንዱና ወሳኝ የምርጫ  ጊዜ ተግባር…
2021-06-18
ግዙፍ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች የሚያመርተውና የሚከፋፈለው ቶታል ኩባንያ የስያሜ ለውጥ አደረገ፡፡ ቶታል ከእንግዲህ በኋላ…
2021-06-18
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገሬ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ንግግርም ሆነ ግጭት ዝግጁ ነኝ አሉ፡፡ የኬም ጆንግ ኡን…
2021-06-18
በመጪው ሰኞ የሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን…