የውጭ ወሬ

መጋቢት 1፣ 2013/ በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብአዊ ኪሳራና አለመረጋጋት የትግራይ ክልልን ሲመራ የነበረው ህወሓት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ለድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በፃፈው የውስጥ ማስታወሻ ይፋ አደረገ

በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብአዊ ኪሳራና አለመረጋጋት የትግራይ ክልልን ሲመራ የነበረው ህወሓት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ለድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በፃፈው የውስጥ ማስታወሻ ይፋ አደረገ።

ይህንኑ ምስጢራዊ ማስታወሻ እንዳገኘው የገለፀው ፎሬይን ፖሊሲ መፅሄት እንደፃፈው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ አኪም ስቴይነር በምሥራቅ አፍሪካ ደም አፋሳሽ ግጭት ሊፈጠር የቻለው ኢትዮጵያን ላለፉት 30 ዓመታት ሲመራ የነበረው የህወሓት አመራር በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመፈፀም የፌደራል መንግሥቱን በመተንኮሱ ነው ብሏል።

የትኛውም አገር ወታደራዊ ጥቃት ሲደርስበት የአፀፋ ምላሽ እንደሚሰጥ የታወቀ መሆኑን ይኸው የውስጥ ማስታወሻ መጥቀሱን ፎሬይን ፖሊሲ ጽፏል፡፡ 

ምላሽ

ጥር 12፣2013/ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ

የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡

ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ጥር 12፣2013 በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የውሳኔ ሂደት፦

1ኛ መሣሪያው በሌላ ሕገ ወጥ መንገድ ያልተገኘና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በአቃቤ ሕግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፤

ምላሽ

ግንቦት 15፣ 2012/ ከሟች ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጊ ቤተሰቦች ተፅፎ የተነበበው የይቅርታ ቃል

ካች አምና ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጊ ቱርክ ኢስታንቡል ወደሚገኘው የሀገሩ የሳዑዲ አረብያ ቆንስላ ጎራ አለ:: የሚፈጽመውን ጉዳይ ጨርሶ ግን አልወጣም:: የእርሱ ራሱ የህይወቱ ፍፃሜ እዛው ሆነ እንጂ፡፡

መቃቃር ከመምጣቱ ቀድሞ ጋዜጠኛው የሳዑዲ አረብያ ንጉሳዊ ቤተሰብ የቅርብ ሰው ነበር፡፡ ከመቃቃሩ ወዲህ መሰረታቸው አሜሪካ በሆኑ ጋዜጦች ላይ ይፅፍ ጀመር፡፡ በተለይ በዋሽንግተን ፖስት ዓምደኝነቱ ይበልጥ ስሙ ገነነ፡፡

ስሙ እና ዘገባዎቹ ከፍ ያለ ትኩረት እያገኙ የመጡትም በሳዑዲ መንግሥት በተለይም በአልጋ ወራሹ መሀመድ ቢን ሳልማን ላይ የሰሉ ትችቶችን መሰንዘር ከጀመረ በሁዋላ ነው፡፡

ምላሽ

ጥር 18፣ 2014- በኢራን በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ነበር የተባለ ፈረንሳዊ የ8 ዓመት ከ8 ወራት የእስር ቅጣት ተፈረደበት

በኢራን በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ነበር የተባለ ፈረንሳዊ የ8 ዓመት ከ8 ወራት የእስር ቅጣት ተፈረደበት፡፡ ግለሰቡ በኢራን እና በቱርክ ሜንስታን ወሰን በበርሃማ ሥፍራ የተያዘው ከዓመት ከ8 ወራት በፊት እንደነበር ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡

ሰውየው ሲያበራት የነበረችው ሂሊኮፕተር በአውቶማቲካዊ መላ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የመቅረፅ ችሎታ ያላት ነች ተብሏል፡፡ ግለሰቡ የቀረበበትን የስለላ ክስ ማስተባበሉ ተሰምቷል፡፡

ጠበቆቹ ክሱም ሆነ በደንበኛቸው ላይ የተላለፈው የእስር ቅጣት ውሳኔ ፖለቲካዊ ነው ብለዋል፡፡ የግለሰቡ የቤተሰብ አባላት ውሳኔውን በመቃወም በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የኢራን የፍትህ ሚኒስቴር ሹሞች በዚህ ጉዳይ አስተያየት እንዳልሰጡ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ምላሽ

ጥር 18፣ 2014- ማዳጋስካርን በመታው አውሎ ነፋስ ከ30 በላይ ሰዎችን መግደሉ ተሰማ

ማዳጋስካርን በመታው አውሎ ነፋስ ከ30 በላይ ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡ ይኸው አውሎ ነፋስ በሞዛምቢክም 3 ሰዎችን እንደገደለ አል አረቢያ ፅፏል፡፡

በማላዊ ደግሞ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ማቋረጡ ተሰምቷል፡፡ በማዳጋስካር አካባቢ የተቀሰቀሰው አውሎ ነፋስ በዶፍ ዝናብ ጭምር የታገዘ ነው ተብሏል፡፡

በማዳጋስካሯ ርዕሰ ከተማ አንታናናሪቮ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ማድረሱ ታውቋል፡፡ አውሎ ነፋሱ በማዳጋስካር በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ቤት አልባ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡

ብዙዎችንም አደጋ ከሚያሰጋቸው አካባቢዎች ማውጣቱ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡ ቀጠናው የአውሎ ነፋስ አደጋ እንደሚደጋገምበት መረጃው አስታውሷል፡፡

ምላሽ

ጥር 18፣ 2014- በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ብዛት በጣሙን እያሻቀበ ነው ተባለ

በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ብዛት በጣሙን እያሻቀበ ነው ተባለ፡፡ በአገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን CGTN ፅፏል፡፡

አጋጣሚው ዕለቱን በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ብዛት የምንግዜውም ከፍተኛው አድርጎታል፡፡ የቫይረሱ ሥርጭት የከፋው ኦሚክሮን በተሰኘው ልውጥ ዝርያ ምክንያት እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

በወረርሽኙ አድማስ መስፋት የተነሳ በአሁኑ ወቅት ከ30000 በላይ ሰዎች ሆስፒታል ለመግባት ተገድደዋል ተብሏል፡፡ ከነዚህም መካከል 4000 ያህሉ በፅኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍሎች መግባታቸው ታውቋል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በበሽታው የ364 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መረጃው አስታውሷል፡፡

ምላሽ

ጥር 17፣ 2014- የማላዊው ፕሬዝዳንት ላዛረስ ቻክዌራ ካቢኔውን እንዳለ ከኃላፊነት ማሰናበታቸው ተሰማ

የማላዊው ፕሬዝዳንት ላዛረስ ቻክዌራ ካቢኔውን እንዳለ ከኃላፊነት ማሰናበታቸው ተሰማ፡፡ በሀላፊነት ላይ የነበሩ 3 ሚኒስትሮች ምዝበራ ሲፈፅሙ ተደርሶባቸዋል መባሉ ለካቢኔው እንዳለ መባረር ለፕሬዝዳንቱ እርምጃ መነሻ እንደሆነ ታይምስ ላይቭ ፅፏል፡፡

በምዝበራ የተጠረጠሩት ሚኒስትሮች ከመሬት ሽያጭ እና ግዢ አግባብ ያልሆነ ጥቅም አግኝተዋል ተብለው ስማቸው በክፉ መነሳቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ ፕሬዝዳንት ቻክዌራ በመንግስት ሹሞች የሚፈፀምን ሕገ-ወጥነት በጭራሽ አልታገስም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ሹሞቹን ከሃላፊነት በተባረሩ በ48 ሰዓታት ጊዜ አዲስ ካቢኔ እሰይማለሁ ብለዋል፡፡

ምላሽ

ጥር 17፣ 2014- በካሜሩን ርዕሰ ከተማ ያውንዴ ወደ ኦሌምቤ ስታዲዮም ለመግባት በተፈጠረ ተገፋፍቶ መረጋገጥ በጥቂቱ 8 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

በካሜሩን ርዕሰ ከተማ ያውንዴ ወደ ኦሌምቤ ስታዲዮም ለመግባት በተፈጠረ ተገፋፍቶ መረጋገጥ በጥቂቱ 8 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡ በአደጋው ከሞቱት ሌላ 40 ያህሉ ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው የእስራኤሉ አርቱዝ ሼቫ ፅፏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድሮችን እያስተናገደች መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስታዲየሙ መግቢያ ተገፋፍቶ በመረጋገጥ አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው ወደ አቅራቢያው ሆስፒታል መወሰዳቸው ተነግሯል፡፡

ተገፋፍቶ መረጋገጥ የደረሰበት ስታዲዮም 60,000 ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም አለው ተብሏል፡፡ በጊዜው ግን ወደ ስታዲየሙ የገቡት ከ50,000 እንደማይበልጡ መረጃው አስታውሷል፡፡

ተገፋፍቶ የመረጋገጥ አደጋውን ያስከተለው ምክንያት ለጊዜው በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡

ምላሽ

ጥር 17፣ 2014- በቡርኪናፋሶ በመንግስት ላይ አምፀው የተነሱት ወታደሮች ሥልጣን መጨበጣቸውን ተናገሩ

በቡርኪናፋሶ በመንግስት ላይ አምፀው የተነሱት ወታደሮች ሥልጣን መጨበጣቸውን ተናገሩ፡፡

የአርበኞች ግምባር የተሰኘው የወታደሮቹ ስብስብ ቃል አቀባይ ወታደሮቹ ትናንት ማምሻውን በመገናኛ ብዙኃን የፕሬዝዳንት ማርክ ሮች ክርስቲያን ካቦሬን መንግስት መገልበጣቸውን እንደተናገሩ CGTN ፅፏል፡፡

ሕገ መንግስቱንም አሽቀንጥረው መጣላቸው ተሰምቷል፡፡ ወታደሮቹ ከፕሬዝዳንት ካቦሬ በተጨማሪ የፓርላማውን አፈ ጉባኤ እና ሌሎች ሹሞችን ሰብስበው ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ርዕሰ ከተማዋ ዋጋዱጉን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እሁድ እለት ከባድ ተኩስ ሲሰማ ነበር ተብሏል፡፡ ትናንትም በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ ተኩስ እንደነበር በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ምላሽ
2022-01-28
በኢትዮጵያ የቡና ግብይት ውስጥ የደላሎች ሰንሰለት በመሰበሩ ከቡና የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተሰማ…
2022-01-28
ሙሉ ገቢው ለተፈናቃይ ወገኖች የሚውል የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይመረቃል፡፡ አዘጋጁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ነው፡፡
2022-01-28
የውሃ ልማት ፈንድ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ለጤና አጠባበቅ አገልግሎት ማሻሻያ ብድር ያቀረብኩላቸው ከተሞች ብድሩን…
2022-01-28
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌአለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ…