የአገር ውስጥ ወሬ

ጥር 20፣ 2014- የኩላሊት ህሙማንን በገንዘብ ለመደገፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ሊሰናዳ ነው ተባለ

እስትንፋሳቸውን ለማቆየት በወር እስከ 36,000 ብር ወጭ የሚጠይቅ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን የኩላሊት ህሙማን በገንዘብ ለመደገፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ሊሰናዳ ነው ተባለ፡፡

ምላሽ

ጥር 19፣ 2014- ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን ከሰኞ ጥር 23፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተናገረ

ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን ከሰኞ ጥር 23፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተናገረ፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡  

አገልግሎቱ ከሰኞ ጥር 23፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር የተናገረው አገልግሎቱ ተገልጋዮች በትዕግስት ስለጠበቁት ምስጋና አቅርቧል፡፡

ምላሽ

ጥር 18፣ 2014- ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት የተነሳ ምዕራባዊያን ሀገሮች ፊታቸውን ካዞሩባት ከራርመዋል

ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት የተነሳ ምዕራባዊያን ሀገሮች ፊታቸውን ካዞሩባት ከራርመዋል፡፡ ፊት ማዞር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ አግባብ ያልሆነ ጣልቃ ሲገቡ ታይተዋል፡፡ 

ይህ የምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት በአለም አቀፍ ግንኙነት ዐይን ሲታይ ምን መሳይ ነው፡፡ 
 

ምላሽ

ጥር 17፣ 2014- በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካበቢዎች በሸኔ ጥቃት ምክንያት 325,000 ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካበቢዎች በሸኔ ጥቃት ምክንያት 325,000 ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተነገረ። 

ከ5000 በላይ መምህራንም ስራ አጥ ሆነዋል ተብሏል። 

ቡድኑን በስህተት የተቀላቀሉ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ በመንግስት የቀረበው ጥሪ በጎ ምላሽ እያገኘ እንደሚገኝም ሠምተናል። 

ምላሽ

ጥር 17፣ 2014- የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ለ3 ዓመታት ያህል ለጎብኚዎች ዝግ ሆኖ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት መከፈቱ ይታወሳል

የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ለ3 ዓመታት ያህል ለጎብኚዎች ዝግ ሆኖ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት መከፈቱ ይታወሳል፡፡ 

ከዓመት በፊት በቃጠሎ ተጎድቶ የነበረው የፓርኩ ክፍል ከቃጠሎው በፊት ከነበረውም በተሻለ ሁኔታ ላይ መገኘቱን ሸገር ተመልክቷል፡፡ 

ምላሽ

ጥር 16፣ 2014- በሀገራችን ገበያ ውስጥ ምርቶች የተለምዶ የደረጃ ስያሜ አላቸው

በሀገራችን ገበያ ውስጥ ምርቶች የተለምዶ የደረጃ ስያሜ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ጤፍ ሰርገኛ ጤፍ፣ ነጭ ጤፍ ወዘተ.. እየተባለ ሲጠራ ይሰማል፡፡

ግን ነጭ ጤፍን ነጭ ጤፍ የሚያሰኘው ምንድን ነው? ውስጣዊ ይዘቱን በዝርዝር የሚገልፅ ደረጃ የማውጣት አስፈላጊነት እዚህ ላይ ይመጣል፡፡

ምላሽ

ጥር 13፣ 2014- የደቡብ ሱዳኖቹ የሙርሌ ጎሣ አባላት ዘርፈው ህፃናትም አፍነው መውሰድ የየዓመቱ ተግባራቸው ሆኗል

የደቡብ ሱዳኖቹ የሙርሌ ጎሣ አባላት ዘርፈው ህፃናትም አፍነው መውሰድ የየዓመቱ ተግባራቸው ሆኗል፡፡  ትናንት በፈፀሙት ጥቃትም ዜጎችን ገድለዋል ከብቶቻቸውንም ዘርፈዋል፡፡ 

አፍነው የወሰዱትን አንድ ህፃን በ200 ከብት ይሸጡታል ይባላል፡፡ እንዲህ ከዓመት ዓመት የቀጠለውን ጥቃት ለመከላከል ክልሉ ምን እየሰራ ነው?

ምላሽ

ጥር 10፣ 2014- የጥምቀት በዓል በጎንደር ከሌላው ቦታ በተለየ ይደምቃል

የጥምቀት በዓል በጎንደር ከሌላው ቦታ በተለየ ይደምቃል፡፡

በትናንትናው ዕለት የቀደመ ታሪክን ለማስታወስ የንጉስ ግብር የእራት ግብዣ በጎንደር ስለመዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡

ምላሽ

በድሬዳዋ ከተማ የኩላሊት እጥበት ማሽን በመንግስት ሆስፒታል ባለመኖሩ ታማሚዎች ለከፍተኛ ወጪና እንግልት እየተጋለጥን ነው አሉ

በድሬዳዋ ከተማ የኩላሊት እጥበት ማሽን በመንግስት ሆስፒታል ባለመኖሩ ታማሚዎች ለከፍተኛ ወጪና እንግልት እየተጋለጥን ነው አሉ፡፡

በከተማዋ ያለው የኩላሊት እጥበት ማሽን አንድ እሱም በግል ሆስፒታል የሚገኝ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የታማሚ ቤተሰቦች ለአንዴ እጥበት 3,500 ብር እንደሚያወጡና ይህን በሳምንት 3 ጊዜ ማድረግ የማይችሉ ሰዎች አማራጭ በማጣት ለህልፈት እንደሚዳረጉ ነግረውናል፡፡  

ይህንን ችግር ለማቃለል የድሬዳዋ ተወላጆች በውጪም በሀገር ውስጥም ያሉ በመንግስት ሆስፒታል የእጥበት ማሽኑን ገዝቶ ለማስገባት ጥር 14 ቀን በድሬዳዋ ራስ ሆቴል የሚዘጋጀውን የእራት ግብዣን ጨምሮ የተለያዩ ገቢ ማስገኛ ዝግጅቶችን አሰናድተው ገቢ እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡

ምላሽ
2022-01-28
በኢትዮጵያ የቡና ግብይት ውስጥ የደላሎች ሰንሰለት በመሰበሩ ከቡና የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተሰማ…
2022-01-28
ሙሉ ገቢው ለተፈናቃይ ወገኖች የሚውል የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይመረቃል፡፡ አዘጋጁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ነው፡፡
2022-01-28
የውሃ ልማት ፈንድ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ለጤና አጠባበቅ አገልግሎት ማሻሻያ ብድር ያቀረብኩላቸው ከተሞች ብድሩን…
2022-01-28
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌአለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ…