በሴቶች ተይዘው የነበሩ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች ተመልሰው በወንዶች እየተያዙ መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read
ህዳር 2 2018
ሴቶች በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲወያዩ፣ መፍትሄም እንዲሰጡ የማድረግ ጅምሮች ቢኖሩም አሁንም ብዙ እንደሚቀር ጥናት አሳየ፡፡
በሴቶች ተይዘው የነበሩ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች ተመልሰው በወንዶች እየተያዙ መሆኑን በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡
ላለፉት 25 ዓመታት ሴቶች በሰላምና ደህንነት ላይ የነበራቸው ተሳትፎና ሚና ምን ይመስላል የሚለው ጥናት ያደረጉት በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን በመስራት ላይ የሚገኙት አቶ መብራቱ ጌርጌሶ ናቸው፡፡
አሁን ላይ ሴቶች በፖለቲካው በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እየተሳተፉ ቢሆንም በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህርት የሆኑት ሙሉእመቤት ማጆሮ(ዶ/ር) ሴቶች በባህላዊ የሰላም ግንባታ ላይ ተሳትፎቸው ምን ይመስላል የሚለው ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በባህላዊ የሰላም ግንባታ ላይ የከፍተኛ ሚና ቢኖራቸውም እንደሰሩ አይቆጠርላቸውም ሲሉ ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments