top of page

30፣2016 - ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት ይፋ አደረገ

ባንኩ ነባሩን የንግድ ምልክት እና መገለጫ የቀየረው በተለየ መልኩ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት እና ለእድገት እና ለፈጠራ ያለውን ትጋት ለማስረዳት በማሰብ ነው ተብሏል።


የባንኩን አዲስ መለያ የተዘጋጀው በአቶ ያየህይራድ ታደሰ እና በስቱዲዮኔት እንደሆነ ተነግሯል፡፡


ለስራውም 7 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል።


አዲሱ የንግድ ምልክት የዓባይ ወንዝ ዋና መገለጫ ከሆነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ የተነሳ እና በሰባት አራት ማዕዘናዊ ቋሚ መስመሮች የተወከለ መሆኑን ተጠቅሷል።


ይህም የባንኩን እድገት፣ ችግሮችን የመቋቋም አቅም፣ አስተማማኘነት እና ታማኘነት ያመለክታል ሲባል ሰምተናል፡፡

የባንኩ የመለያ መገለጫ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ታማኝ አገልጋይ ወደ "Source of Greatness" መቀየሩንም ሰምተናል።


የእንግሊዝኛው አቻ የአማርኛ ፍቺም እየታሰሰበት ነው ተብሏል።



አዲሱ የንግድ ምልክት መገለጫው የደንበኞቹ ትልቅ የመሆን ተስፋ፣ ምኞት እና እቅድ ምንጭ በመሆን፤ ወደ ከፍታ ለመድረስ በሚደረግ ጉዞ የማያለሰልስ የባንኩን የፋይናንስ ድጋፍ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ሀብቱ 60 ቢሊዮን ብር፣ የተቀማጭ 48.6 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታል 5.8 ቢሊዮን ብር ፣ አጠቃላይ ካፒታሉ 8.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል።


ከ533 በላይ ቅርንጫፎች እና 3.2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችም አሉኝ ብሏል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Kommentare


bottom of page