top of page

ጳጉሜ 5፣2016 - በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች 94.6 ከመቶ ተማሪዎች ማለፍ አልቻሉም

  • sheger1021fm
  • Sep 10, 2024
  • 1 min read

በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 94.6 ከመቶ ተማሪዎች ማለፍ አልቻሉም።


ያለፉ ተማሪዎች 5.4 ከመቶ ብቻ ናቸው።


የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ፣ በዚህ ዓመት 684,000 ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠው ነበር።


ከዚህ ውስጥ 36,409 ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማልፊያ ውጤት አምጥተዋል።

የማለፊያ ነጥብ ካመጡት መካከል 10,600 ወይም 21 ከመቶ የሚሆኑት የአዲስ አበባ ተማሪዎች ናቸው።


ከአዲስ አበባ የመንግስት ት/ቤቶች 3.3 ከመቶ ተማሪ አሳልፈዋል ተብሏል፡፡


በዚህ ዓመት 1,221 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከ600 ከፍተኛው ውጤት 575 በተፈጥሮ ሳይንስ 538 ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ እንደተገኘ ተሰምቷል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች መካከል 1,363 ት/ቤቶች አንድም ተማሪ አላለፉባቸውም ተብሏል፡፡


የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል ተብሏል።


በረከት አካሉ

Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page