በሀገር ውስጥ እና ድንበር ተሻግረው በሚገቡ ታጣቂዎች ምክንያት ያለኝን የወርቅ ሃብት አውጥቼ መጠቀም አልቻልኩም ሲል የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ተናገረ፡፡
ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ያለባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በመኖሩ ወርቁን አውጥቶ መጠቀም አልቻልኩም ሲል ክልሉ ተናግሯል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የማዕድን እና ኢነርጂ ኤጀንሲ ቢሮ ዳይሬክተር ገብረማሪያም ሰጠኝ በአገር ውስጥ እና ድንበር ተሻግረው በሚገቡ ታጣቂዎች ምክንያት በክልሉ ያለውን የወርቅ ሃብት በሚገባ መጠቀም አልተቻልም ብለዋል፡፡
የጸጥታ ችግር ያለባቸው የክልሉ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን እና ጥራት ያለው ወርቅ ነው የሚገኘው ሲሉም ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡
ከደቡብ ሱዳን እና ከኬንያ የሚገቡ ታጣቂዎች ወርቁ ተመርቶ ለአገርም ለአካበቢውም ማህበረሰብ እንዳይበጅ እንቅፋት ሆነዋልም ብለዋል አቶ ገብረማሪያም ሰጠኝ፡፡
«በምዕራብ ኦሞ ዞን ማጂ ወረዳ ጥራቱ ከፍ ያለ ከ23 እስከ 24 ካራት የሚሆን ወርቅ ኮሉ እና ዲካስ በሚባሉ ቦታዎች አለ ግን አሁን ሙሉ በሙሉ በአርብቶ አደሮች መካካል በሚፈጠር ግጭት ማልማት አልተቻለም» ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የማዕድን እና ኢነርጂ ኤጀንሲ ቢሮ ዳይሬከተር ገብረማሪያም ሰጠኝ ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም «ሚኒት እና ጎሪ ጌሻ የሚባሉት አካባቢዎች ወርቅ ያለባቸው ናቸው ከአርብቶ አደሮች ጋር ሰለሚዋሰኑ የጸጥታ ችግር አለባቸው እዚያም ማልማት አልተቻለም ሲሉ ዳይሬክተሩ ነገረውናል፡፡
ተያያዥ ዘገባ…. https://tinyurl.com/yc5w2kmf
ያሬድ እንዳሻው
Comments