top of page

ጳጉሜ 5፣2016 - ሕብረት ኢንሹራንስ ከምስረታው ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረውን መለያ(ብራንድ) በአዲስ ቀየረ።

ኩባንያው ላለፉት 30 ዓመታት ሲገለገልበት የነበረውን መለያ ዘመኑን በዋጀ እና አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መቀየሩን አስረድቷል።


የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወንድወሰን ተሾመ ነባሩን መለያ መለወጥ ያስፈለገበት ምክንያት "በሰላሳ ዓመት እና በዛሬ መካከል ሰፋ ያለ የጊዜ ልዩነት በመኖሩ ምክንያት እና ዓለም ደግሞ በፈጣን ለውጦች የተሞላች ነገሮችም በአጭር ጊዜ የሚለዋወጡ ከመሆናቸው አኳያ ዘመኑን የዋጀ ቀላል፣ ዘመናዊ፣ በአዕምሮ ውስጥ ታትሞ የሚቀመጥ፣ በጊዜ መለወጥ የማይደበዝዝ፣ ማራኪ  እና የመሳሰሉትን የሚያሟላ መለያ በማስፈለጉ ነው" ብለዋል።


አዲሱ የሕብረት ኢንሹራንስ መለያ የኩባንያው ዋነኛ መለያ ባህሪያት የሆኑትን ሕብረትን፣ ብዙሃነትን፣ ጥንካሬን፣ ያልተቋረጠ ዕድገትን፣ ልህቀትን እና የመሳሰሉትን የሚገልፅ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡

የኩባንያው አዲስ መለያ  የተዘጋጀው በአቶ ያየህይራድ ታደሰ እና በስቱዲዮኔት እንደሆነ ሰምተናል፡፡


በሕብረት ኢንሹራንስ አዲስ መለያ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት ላይ  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ሱፐርቪዥን  ዳይሬክተር እና የኢንሹራንሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተገኝተዋል።


ኩባንያው  የተመዘገበ 1.5 ቢሊዮን ብር እና የተከፈለ 1.067 ቢሊዮን ብር ካፒል እንዳለው አስረድቷል።


ጠቅላላ ሀብቱም ወደ ብር 4.5 ቢሊዮን አድጓል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page