top of page

ጳጉሜ 4 2017 በኢትዮጵያ ከ2,500 በላይ ከተሞች ቢኖሩም የከተማ አስተዳደር ደረጃ የደረሱት ግን 275ቱ ብቻ መሆናቸው ተነግሯል።

  • sheger1021fm
  • Sep 9
  • 2 min read

Updated: Sep 10


ቀሪዎቹ ከ2,000 በላይ ከተሞች ገና በማዘጋጃ ቤት ደረጃ ያሉ ናቸው ተብሏል።


እንደ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ከአስር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የነበሩ ከተሞች ከ1000 አይበልጡም።


አሁን ላይ ግን በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች 2543 እንደሆኑ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ree

ቀሪዎቹ ከ2000 በላይ ከተሞች ገና በማዘጋጃ ቤት ደረጃ ያሉ መሆናቸውን ጠቅሷል።


ሠፊ የሆነ የክትመት ምጣኔ መኖሩን መረጃው ያሳያል።


የከተሞች ፈጣን በሆነ መንገድ ወደ ጎን መስፋት ዘርፈ ብዙ ችግር እያስከተለ እንደሚገኝ ተነግሯል።


የመሬት አያያዝ ችግር አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።


አሁንም እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ያሉት 2543 ከተሞች ከሚይዙት ስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊየን ቁራጭ መሬት መመዝገብ የተቻለው 30 በመቶውን ብቻ ነው።


በእነዚህ ከተሞች ከሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ከ40 እስከ 70 በመቶ የሚደርሱት ከደረጃ በታች እና ህገ ወጥ በመሆነ መንገድ በተያዘ ቦታ ላይ የተገነቡ ናቸው ተብሏል።


ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ የ27 በመቶው መኖሪያ ናቸው የሚባሉት ከተሞች በአብዛኛው ገና በማዘጋጃ ቤት ደረጃ የመገኘታቸው ምክንያት ምን ይሆን? 


መጀመሪያ ላይ የታሰበው በፌዴራል ደረጃ መስፈር ወጥቶ ከተሞች እንዲደራጁ ነበር የሚሉት የከተማ ልማት ባለሞያው አቶ ሚብራስ መሃመድ፤

በኋላ ግን ክልሎች  የራሳቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ያስገባ መስፈርት አውጥተው መስራት እንደጀመሩ ይናገራሉ።


በኢትዮጵያ ከተሞች ከሀገሪቱ አጠቃላይ ስፋትም ዐ ነጥብ 6 ስኩዌር ካሬ ኪሎ ሜትሩን ይይዛሉ።

በዚህ መሬት ላይ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ 27 በመቶ የሚሆነውን ያኖራሉ።


ዓመታዊ የህዝብ ዕድገታቸው ደግሞ 5 ነጥብ 4 በመቶ እንደሆነ ቀደም ብለን የጠቀስነው ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።


በአለም ላይ ፈጣን ከሚባሉት የህዝብ ቁጥር ዕድገት መካከል እንደሆነም ይጠቅሳል

በከተሞች የሚኖረው ሰው ቁጥር መብዛቱ በራሱ ጥሩ ነው የሚሉት ባለሞያው አቶ ሚብራስ ዕድገቱ እንዴት ነው የመጣው የሚለውም አብሮ አብሮ ሊታይ እንደሚገባው ግን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ከተሞች ለጥቅል ሀገራዊ ምርት የሚያበረክቱት ድርሻም ከፍ ያለ ነው።


አሁን ላይ እስከ 55 በመቶ ድርሻ ለጥቅል ሀገራዊ ምርት እንደሚያበረክቱ ተነግሯል።


ትክክለኛውን መንገድ ተከትለው ቢስፋፉ ደግሞ ይህ ድርሻቸው ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።


ከተሞች ባልተፈለገ መልኩ ወደ ጎን እንዲሰፉ የሚያደርገው አንዱ ምክንያት ፍልሰት በመሆኑ እሱ ላይም መስራት ይገባል ተብሏል።

      

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page