top of page

ጳጉሜ 4፣2016 - የላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች ጷጉሜን ለወገናችን ደም እንስጥ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

  • sheger1021fm
  • Sep 9, 2024
  • 1 min read

የላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች ጷጉሜን ለወገናችን ደም እንስጥ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።


የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃግብር አካሄደዋል፡፡


በዚህ ዓመት ለ4ተኛ ጊዜ በተካሄደው የደም ልገሳ መርሀ ግብሩን 120 የሆስፒታሉ ሰራተኞች ደም መለገሳቸውን ሰምተናል፡፡

ላንሴት ላለፉት 3 ዓመታት በየ 3ወሩ በሚያካሄደው መርሃግብር የማዕከሉ ሰራተኞችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ አካላትን በማስተባበር ደም እንዲለግሱ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡


ይህ የ2016 ዓ.ም 4ተኛ ዙሩንም እንኳን አደረሳቸው በማለት የደም ልፈገሳ መርሀ ግብሩን አካሂዷል፡፡


በዚህ የደም ልገሳ መርሀ ግብር የላንሴት ሰራተኞች፣ ታማሚ ጠያቂዎች እንዲሁም የተለያዩ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


‘’ደም በመለገስ ክቡርን የሆነውን የሰውን ነፍስ እንታደግ’’ ሲል ሆስፒታሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page