አምና በነሐሴ ወር የተቀሰቀሰው የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት የሰው ህይወት እየቀጠፈ፣ እያፈናቀለ፣ ንብረት እያወደመ ዛሬም ቀጥሏል፡፡
በክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስር ወራት ለመተዳደርም ተገዶ አልፏል፡፡
የንግግር፣ የውይይት ጉዳዮች እስካሁን በክልሉ የጥይት ድምፅ እንዳይሰማ የማድረግ እድል አላገኙም ክልሉ 2016 ዓ.ም እንዴት እያገባደደው ነው?
በአመቱ ውስጥ መንግስትንና የትጥቅ ትግል እያካሄደ ያለውን አካል በጠረጴዛ ዙሪያ ለማነጋገር እና ችግሩ በድርድር እንዲያልቅ ለማድረግ ከአንድም ሁለት አካላት ጥረት ጀመረው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና በክልሉ የተቋቋመው የሰላም ካውንስል የጀመሩት የእናቀራርባለን፣ እናነጋግራለን እቅድ የት ደረሰ?
ሌሎችስ ከግጭቱ ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ነበሩ?
ትዕግስት ዘሪሁን
留言