top of page

ጳጉሜ 1 2017 - በግብርና ዘርፍ ሚሰሩ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚደረግላቸው ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው፣ ወጣቶች በዘርፉ ባለቸው አቅም ልክ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Sep 6
  • 2 min read

በግብርና ዘርፍ ሚሰሩ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚደረግላቸው ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው፣ ወጣቶች በዘርፉ ባለቸው አቅም ልክ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል ተባለ፡፡


የግብርና ዘርፍን ለማሻሻል እና አሰራሩን የሚያቀልሉ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት አዳዲስ ሀሳብና ተነሳሽነት ያላቸው ወጣቶች በኢትዮጵያ ቢኖሩም በተለይ በፋይናንስ በኩል የሚደግፋቸው ባለመኖሩ የፈጠራ ሀሳባቸው በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንዳልተቻለ ተነግሯል፡፡


ወጣቶቹ የፈጠራ ሀሳቦቻቸውን ፈትሾ አዋጭ የሆኑት ተቀብሎ ወደስራ እንዲገቡ መንግስትም ሆነ የሚመለከታቸው ድጋፍ ሊያድርጉላቸው እንደሚገባም ተነግሯል፡፡


ይህ የተነገረው ‘’የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር’’ (Youth in Agroecology Startup Competition) አሸናፊዎች የሽልማት ሥነ ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ree

የዚህ ውድድር አላማም፤ የምግብ ሉዓላዊነት፣ ዘላቂያዊነት፣ ለማኅበረሰብ ደህንነት ሀገር በቀል መፍትሔዎችን ማምጣት እና ጤናማ ሀገር በቀል ምግቦችን ማስተዋወቅ እንደሆነ በመድረኩ ሲነገር ሰምተናል፡፡


በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢኖቬሽን እና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኃላፊ የሆኑት ብርሃኑ አደሬ፤ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ተናግረው፤ መንግስት የፋይናንስ ተቋማት እንዲደግፏቸው እየሰራን ነው፤ በቂ የሚባል ግን አይደልም ሲሉ በመድረኩ ተናግረዋል፡፡፡፡


በምግብ ደህንነት እና ግብርና ዘርፍ የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች በጣም አነስተኛ እንደኑ የጠቀሱትና በዚህ ዘርፍ ወጣቶች ድጋፍ ቢደረግላቸው በተለይ በምግብ ደህንነት እና ዋስትና ላይ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ሲሉም በመድረኩ የተናገሩት ‘’የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓትና ሥነ ምሕዳራዊ ግብርና ሕብረት ዋና ሥራ አስኪያጅ ባዩሽ ጸጋዬ(ዶ/ር) ናቸው፡፡


የአፍሪካ ምግብ ሉዓላዊነት ሕብረት ዋና ዳይሬክተር ሚሊዮን በላይ(ዶ/ር)፤ ወጣቶች በተለይ በግብርናው ዘርፍ ያተኮሩ ፈጣራዎች ላይ ወደ ተግባር እንዲገቡ ቢደረግ በምግብ ሉአላዊነት እና ዋስትና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለቸው አስረድተዋል፡፡

ree

‘’በወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር’’ የፈጠራ ሀሳቦቻቸው ካቀረቡ 54 ወጣቶች መካከል በዘርፉ ልምድ ባላቸው ዳኞች ተመዝነው ለተመረጡት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም አንደኛ ለወጣው ኪሩቤል ኃይለሥላሴ 200,000 ብር፣ ሁለተኛ ለወጣው ዳግማዊ አመሃ 150,000 ብር እና ሦስተኛ ለወጡት ሕይወት ሲሳይ እና ኢማን ኢብራሂም 100,000 ብር ተሸልመዋል።


ይህ ውድድር፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓትና ሥነ-ምሕዳራዊ ግብርና ሕብረት (Ethiopian Sustainable Food Systems and Agroecology Consortium - ESFSAC) ከየአፍሪካ ምግብ ሉዓላዊነት ሕብረት (Alliance for Food Sovereignty in Africa - AFSA) በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page