ጳጉሜ 1፣2016 - የፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት እሁድ ጷጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይፈጸማል
- sheger1021fm
- Sep 6, 2024
- 1 min read
የአደባባይ ምሁሩ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ የቀብር ስነስርዓት የሚፈጸመው በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል፡፡
በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት ባስተማሩበትና በሰሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ራስ መኰንን አዳራሽ የስንበት ስነ-ስርዓትም ይከናወናል፡፡
ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ በተወለዱ 79 ዓመታቸው ባለፈው ሀሙስ አመሻሽ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ማን ነበሩ?
Comments