top of page

ጳጉሜ 1፣2016 - የከፍታ ወጣቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር(ሳኮ) በብሔራዊ ደረጃ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የከፍታ ወጣቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር(ሳኮ) በብሔራዊ ደረጃ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።


"ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም" ወጣቶችን በኢኮኖሚ በመጥቀም በኩል ትልቅ ምዕራፍ ይከፍታል የተባለለትን በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመውን የከፍታ የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበርን በይፋ ማስጀመሩን በዛሬው ዕለት ተናግሯል።


በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ(USAID) የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበረው ''ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም"፤ ወጣቶች በአነስተኛ የወለድ ብድር ወስደው ስራ እንዲጀምሩ፣ የጀመሩ ካሉም ስራቸውን የሚያሳድጉበት እና ትርፋማ የሚሆኑበትን እድል የሚፈጥር መሆኑ ተነግሮለታል።


ይህ በብሔራዊ ደረጃ ተመዝግቦ እውቅና የተሰጠው የከፍታ የወጣቶች ብድርና ቁጠባ ከ7,800 በላይ አባላት እንዳሉት ሰምተናል።


ከ38,900 በላይ አክሲዮኖችን የሸጠ እና ወደ 6ዐ ሚሊዮን ብር በቁጠባ ሰብስቦ በአነስተኛ ወለድ ለወጣቶች በማበደረ ላይ የሚገኝ  መሆኑም ተነግሯል።


በዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመው የከፍታ ወጣቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር(ሳኮ) የኢትዮጵያ ወጣቶችን የፋይናንስ ተደራሽነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚሰራ፣ በወጣቶች የሚመራ፣ በወጣቶች የተደራጀ እና በወጣቶች የሚተዳደር ተቋም ነው።


የከፍታ ወጣቶች ሳኮ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመና በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ የወጣቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ሲሆን፤ በ15 የከፍታ ፕሮጀክት ከተሞች ውስጥ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉት ተብሏል።


ከ18 እስከ 35 ዓመት እድሜ ያላቸው ወጣቶች፣ ዝቅተኛውን 1,000.ዐዐ ብር (4 አክሲዮኖች በ 250.00 ብር እያንዳንዳቸው )፣ የአንድ ጊዜ የመመዝገቢያ ክፍያ 200.00 ብር፣ እና የግዴታ ወርሃዊ ቁጠባ 300.00 ብር ለመግዛት ፍላጎት እና ችሎታ ያላቸው አባል መሆን  ይችላሉ ተብሏል።


የከፍታ ወጣቶችን ሳኮ ዝቅተኛ የብድር ወለድ እና ለወጣቶች ተስማሚ ሆኖ መገኘቱ፣ በአጭር ጊዜ ተከታታይ ቁጠባ በኋላ ብድር ለመጠየቅ ብቁነት የሚያደርግ መሆኑ፣ ረዘም ያለ የብድር መክፈያ ጊዜ መስጠቱ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት የሚለይባቸው ባህሪዎቹ ናቸው ተብሏል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page