top of page

ጳጉሜ 1፣2016 - የትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ለማድረግ እየተዘጋጀሁ ነው አለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Sep 6, 2024
  • 1 min read

ስርዓተ ትምህርት ክለሳው የሚደረገው ተማሪው የሚማራቸው የትምህርት ዓይነቶች ምን ያህል ተረድቷቸዋል የሚለው ለመለካት ነው ተብሏል፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና(ዶ/ር) ተማሪዎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


በተለይም አሁን የቴክኖሎጂ ዘመን በመሆኑ ትውልዱ በቅጡ ይህንን የተገነዘበ እንዲሆን መደረግ አለበት ይላሉ፡፡


አንድ ተማሪ ትምህርት ሲማር የተማረውን ምን ያህል ተገንዝቦታል በዚህስ ብቁ ሆኗል ወይ? የሚለውን ለመገንዘብ እንዲያመች ተደርጎ አሁን ያለው ስርዓተ ትምህርት ለማሻሻል የሚረዳ የአፈፃፀም መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ኤባ ከዚህ በፊት አደረግሁት ባሉት ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መምህር ለተማሪው ከ100 ከ70 በታች ውጤት ከሰጠው ወደቀ የሚባለው መምህሩ እንጂ ተማሪው አይደለም፡፡


መምህራን ይህንን ፍራቻ በሚል አንድም ተማሪ ከ70 በታች ሲያመጣ የሚሞሉትን ሞልተው ተማሪው ያላመጣውን ውጤት እንደሚሰጡት በጥናቴ ደርሼበታለሁ ይላሉ፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር አሁን የሚሰጣቸው ፈተናዎች የበዙትም በዚህ መንገድ የመጣውን በሚገባ ለማጣራት ይረዳል ለዚህም ነው ፈተናዎቹ የበዙት ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


የትምህርት ጥራት የተሻለ እንዲሆን ፈተናዎችን ከማብዛትም ባለፈ የሚሰጡት ፈተናዎች በዲጂታል እንዲሰጡ እየተደረገ ነው፡፡


ይህም እየሆነ ያለው የፈተና ሌብነትን ለማስቀረትና አቅም ያለው ተማሪ ለማፍራት ነው ይላሉ፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር በየጊዜው የሚያደርጋቸው የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያዎችና በየጊዜው የሚሰጡ የፈተና ዓይነቶች ሀገሪቱ ብቁ ተማሪ እንድታገኝ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡


ተማሪ መለካት ያለበት በሰራው ልክ ሊሆን ይገባል መባሉን ሰምተናል፡፡




በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page