ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ቀዳሚ መሆኗ ቢነገርላትም ስጋው ፣ ቂቤው እንቁላሉና ሌላውም የእንስሳት ተፅዕኖ ዋጋቸው ውድ ከሆነባቸው ሃገራትም ቀዳሚዋ ነች፡፡
እንዲህ ያለው ተቃርኖ ከየት የመጣ ነው? የሚለውን ለማወቅ እና የእንስሳት ሀብቷንና የግብርና ምርት ውጤቶቿን በትክክል ለማወቅ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጥናትና ቆጠራ ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡
የጥናት ውጤቱም የሃገራዊ ጥቅል ምርትን በአግባቡ ለመለካትና የግብርናው ምርት ያለበትን ችግር አውቆ መፍትሄ ለማበጀትም ያግዛል ተብሏል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Comments