የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሻሽሎ ከወራት በፊት ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ የማይከፈልበት የመንግስት አገልግሎት ማግኘት ከባድ ሆኗል፡፡
ለውሃ ፣ ለመብራት፣ ለቴሌኮም አገልግሎትና ለሌላውም ተጠቃሚው 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
አሁን የፋይናንስ ተቋማትም ወደዚሁ ሥርዓት እየገቡ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ከጀመረ ሳምንታት የተቆጠረ ሲሆን ሌሎች ባንኮችም ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡
ለመሆኑ ከቆጣቢዎቻቸው 6 በመቶዎቹን ብቻ የብድር ተጠቃሚ የሚያደርጉት በሚጥሉት ከፍተኛ ወለድም በቢሊየን ትርፍ የሚያጋብሱ የሚባልላቸው ባንኮች በዚሁ ጊዜ ቫት ማስከፈላቸው ትክክል ነው ወይ?
የሚያስከትለውስ ስጋት ምንድነው? የፋይናንስ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comentários