top of page

ጥቅምት 8፣2017 - ችግር ላገኛቸው ሰዎች፣ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ወይም ለአንድ ዓላማ ገቢ ለማሰባሰብ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ችግር ላገኛቸው ሰዎች፣ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ወይም ለአንድ ዓላማ ገቢ ለማሰባሰብ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ።


መተግበሪያው "ሳንቲም ፈንድ ሚ" ይባላል።


ይህንን የኦንላይን የገቢ ማሰባሰቢያ  መላ   ያዘጋጀው፤ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ ነው።


በመተግበሪያው አማካይነት ለጋሾች ለሚፈልጉት ግለሰብ፣ ተቋማት እና ድርጅቶች በኦንላይን  ገንዘብ መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

ሳንቲም ፈንድ ሚ፤ ለለጋሾች  በቀላሉ እና ደህንነቱን በተጠበቀ መልኩ ልገሳ እንዲያደርጉ ያመቻል ሲባል ሰምተናል፡፡


ተጠቃሚዎች ሳንቲም ፈንድሚን ሲጠቀሙ፣ የራሳቸውን የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻዎች ከመፍጠር ባለፈ፣ ግልጽ የገቢ ማሰባሰቢያ ግቦችን በማውጣት ለጋሾች ድጋፋቸዉ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ማሳየት ይችላሉ ተብሏል፡፡


ከዚህ ባለፈም ተጠቃሚዎች የራሳቸዉን የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ማጋራት እንዲችሉ መድረኩ አመቻችቷል ተብሏል።


በየትኛውም የዓለም ማዕዘን ያለ ሰው፣ መተግበሪያውን በስልኩ በመጫን በፕላትፎርሙ ላይ ለገቡ እና ለሚገቡ ድርጅትም ሆነ ግለሰቦች በቀላሉ ገንዘብ መለገስ ይችላል ሲባል ሰምተናል።


ንጋቱ ሙሉ


コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page