ጥቅምት 8፣2017 - ለመሆኑ ስራ እና ሰራተኛ መገናኘት ያልተቻለው ለምንድነው?
- sheger1021fm
- Oct 18, 2024
- 1 min read
በጤና ተቋማት የአንስቴዥያ ህክምና ባለሞያዎች ቁጥር አናሳ መሆኑ ሆስፒታሎች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል።
በሌላ በኩል ግን በዘርፉ የተመረቁ በርካታ ባለሞያዎች ቢኖሩም ስራ አጥ ሆነው መቀመጣቸው ተሰምቷል።
ደረጃውን ለጠበቀ አንድ ሆስፒታል ከ 80 የማያንስ የሰመመን ህክምና ባለሞያዎች ቢያስፈልጉትም አሁን ላይ በየሆስፒታሎች ያሉ ባለሞያዎች ከአንድ የማይበልጡ መሆናቸውንም ሰምተናል።
ለመሆኑ ስራ እና ሰራተኛ መገናኘት ያልተቻለው ለምንድነው?
ፍቅሩ አምባቸው
Comments