ጥቅምት 6፣2017 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 አውሮፕላን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ ተናግሯል
- sheger1021fm
- Oct 16, 2024
- 1 min read
በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 አውሮፕላን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ ተናግሯል።
አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉንም ተጠቅሷል፡፡
አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ መሆኑን አስረድቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
تعليقات