በቡና ምርት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደር ሴቶችን የሚደግፍ ተቋም ባሉበት አካባቢ ባለመኖሩ ምርቱም ላይ ሆነ አምራቾቹን እየጎዳ ነው ተባለ፡፡
ይህ ደግሞ በቡና ምርት ላይ የተሰማሩ ሴቶች ከእርሻ ጀምሮ ቡናው ለገበያ እስኪቀርብ ድርስ የሚኖራቸው ተሳትፎ በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል፡፡
ምርቱን ከማምረት የሚጀምረውን ስራ ሴቶች ቢከውኑም ምርቱ ወደ ገበያ በሚወጣበት ወቅት ግን እንብዛም አይታዩም፡፡
ይህንን ያለው ኢትዮጵያን ውሜን ኢን ኮፊ (Ethiopia women in coffee) አስጠናሁት ባለው ጥናት ነው፡፡
በጥናቱም ሴቶች በቡና ማምረት ዘርፉ ላይ ያላቸው ተሳትፎ እስከ 90 በመቶ ነው ነገር ግን ምርቱ ወደ ገበያው ሲወጣ ተሳትፎአቸው ወደ 70 በመቶ ይወርዳል ተብሏል፡፡
ይህ የሆነው ደግሞ በቡና ምርት ላይ የተሰማሩትን አምራቾች የሚያግዝ ተቋም ባለመኖሩ ነው ይላሉ የ Ethiopia women in coffee ዳይሬክተር የሆኑት ሳራ ይርጋ፡፡
በቡና ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ሴት አምራቾች የሚያግዝ ተቋም አለመኖሩ ከዘርፉ ሀገርም ሆነች አምራቹ ማግኘት ያለበትን ጥቅም ሲያገኝ አይታይም ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡
በዘርፉ ላይ ተሰማርተው ለአምራቾቹ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማት በብዛት የሚገኙት ከተማ አካባ መሆናቸው እና ወደታች ተወርዶ ስር አለመሰራቱን የሚናገሩት ሳራ ይርጋ ይህ ደግሞ በምርቱ ላይ የሚያከትለው ኪሳራ ቀላል አይደለም ይላሉ፡፡
የብድር አቅርቦት ምቹ አለመሆን ደግሞ ቡና አምራች ሴቶችን ወደ ኋላ ከሚጎትታቸው ምክንያቶች መካከል ነው ተብሏል፡፡
በዘርፉ የሚነሱ ችግሮችን ለመቀነስ፣ የቡና አምራች ሴቶች በልፋታቸው ልክ እንዲያገኙ እና ወደ ገበያው እንዲወጡ ለማድረግ ስራ እየከወንኩ ነው ያለው Ethiopia women in coffee ባለፉት ሁለት ዓመታት 150 ለሚሆኑ አምራቾች ስልጠና ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ.. https://tinyurl.com/5de32kma
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments