top of page

ጥቅምት 6፣2016 - ባለፉት 3 ወራት ከቅባት እህሎች የውጪ ንግድ ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱ ተነገረ

በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያዉ የሩብ ዓመት ከቅባት እህሎች የውጪ ንግድ 31 ሚሊዮን 513 የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ከተያዘው የሩብ ዓመት እቅድ አንፃር 79.64 በመቶ ማሳካት ተችላል ተብሏል፡፡


በሩብ ዓመት አፈፃፀሙ በመጠን 17,729 ሜትሪክ ቶን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ነበር የተባለ ሲሆን የእቅዱን 74.87 በመቶ ለገበያ መቅረቡን ተነግሯል፡፡


የግብይት ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የኦንላይን አገልግሎት ሥርዓትን በመዘርጋት የወጪ ኮንትራት ምዝገባ አፈጻጸምና የኤክስፖርት የመላኪያ ፍቃድ አገልግሎቶት አሠጣጥን ወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በተያያዘ ወሬ ከጥራጥሬና ሰብሎች የውጪ ንግድ ባለፉት 3 ወራት 85.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተነግሯል፡፡


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥራጥሬ እና ሰብል ምርት በበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት የውጪ ንግድ ከ85.7 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን ከተያዘው የሩብ ዓመት እቅድ አንፃር 146.24 በመቶ ማሳካት ተችላል፡፡


በሩብ ዓመት አፈፃፀሙ በመጠን 110,221 ሜትሪክ ቶን ለዓለም ገበያ ቀርቦ የእቅዱን 153.2 በመቶ አፈፃፀም አስመዝግቧል ተብሏል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ውጪ ከሚላኩ የወጪ ምርቶች ከቡና እና ከአበባ ምርት ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ የወጪ ምንዛሪ ገቢ የሚገኝበት ዘርፍ ነው፡፡


የዘርፉ የወጪ ንግድ እቅድ አፈፃፀም መጨመር ምክንያቶች በውል እና ኢንቨስትመንት እርሻ የተመረተውን ምርት በተዘረጋው የግብይት መመሪያ መሰረት ላኪ ድርጅቶች በክምችት ሳይዙ በወቅቱ ኮንትራት ገብተው ለአለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ በመቻላቸው መሆኑን ተነግሯል፡፡


ከዚህ ባለፈ ህገ-ወጥ እና ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተጠናከረ ክትትል በመደረጉ የተሻለ ገቢ ማግኘት መቻሉ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡



በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Commentaires


bottom of page