ጥቅምት 5 2018 - የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Oct 15
- 1 min read
ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል።
ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው።
ተቋሙ ከህግ ውጪ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው የሚቆረጥባቸው ገንዘብ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበልኝ ነው ብሏል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ከደመወዛቸው ላይ ገንዘብ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነግረውኛል ብሏል።

በተመሳሳይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞንም በተለያዩ ወረዳዎች የሚሰሩ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተነግሯል።
ይህም የችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል ብሏል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫ።
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ስምምነቱን በፅሁፍ ሲገልፅ፣በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይንም በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ ደሞዙን መቁረጥም ሆነ መያዝ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል ብሏል።
ችግሩ አለ ተብሎ ቅሬታ በቀረበባቸው አካባቢዎችም አስቸኳይ እርምት ሊደረግ ይገባል ሲል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳስቧል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ቴዎድሮስ ወርቁ
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments