top of page

ጥቅምት 5፣2017 - ግሎባል ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቶቼ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ላስረክብ ነው አለ

ባለፈው 2016 ዓመት በሁለት ዙር ለ29 አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ማስረከቡን የሚናገረው ማህበሩ በያዝነው የጥቅምት ወር መጨረሻ ለተጨማሪ 32 አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማስረከብ ህጋዊ ሂደቶችን እያጠናቀቀ መሆኑን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ተናግሯል፡፡


የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባዘዘው የተዘጋጀው የኤሌክትሪክ መኪና ዋጋው 4ሚሊዮን እንደሆነና መኪኖቹን የሚረከቡት የዋጋውን 30 በመቶ ማለትም 1.2 ሚሊዮን ብሩን ለቆጠቡ አባላቱ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡


ኢትዮጵያ ከነዳጅ ይልቅ ፊቷን በኤልክትሪክ ወደሚሰሩ መኪኖች እያዞረች መሆኑን ተከትሎ እንደማህበር ከያዝነው ዓመታዊ እቅድ ከ80 በመቶ በላዩን ገንዘብ ለኤሌክትሪክ መኪና ብድር እየሰጠን ነው ያሉት አቶ ሞላ የኤሌክትሪክ መኪኖች በቻርጅ የሚሰሩ እንደመሆናቸውና አሁን ባለው ሁኔታ በየቦታው ይህ ባለመኖሩ ማህበሩ በራሱ የቻርጅ ማድረጊያ ቦታ እያመቻቸ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት ሲያስቡ የብዙቆች ጭንቀት ቻርጅ አድርጌው ወጥቼ ድንገት አልቆ መንገድ ላይ ቢያስቀረኝስ የሚል ነው፤እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡

አንድ ጊዜ ቻርጅ የሚደረግ መኪና 400 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል፣ በከተማ ውስጥ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ1 ቻርጅ እስከ 3 ቀን መጠቀም እንደሚችሉ ከዚህ ቀደም አስረክበናቸው ወደ ትራንስፖርት ስራው የገቡ መኪኖች ምስክር ናቸው ሱሉ አቶ ሞላ አስረድተዋል፡፡


ግሎባል ቁጠባና ብድር በዘርፉ ተሰማርተው ከሚሰሩ መሰል ተቋማት በምን ይለያል?


ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከ2900 በላዩ አባላት ምንም ያህን የድርሻ መጠን ቢኖረው የትርፉ ተካፋይ ነው፣ ብድር ሲወስድም ከ13 በመቶ ወለድ ነው፣ የሚወስደውን ብድር 30 በመቶ ከቆጠበ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የቤት የመኪናና ሌላውም ብርድ ይሰጠዋል፡፡


ማህበሩን ለመቀላቀል እያንዳንዱ አክሲዮን 1000 ብር ሆኖ ለስራ ማስፋፊያ፣ ለትምህርትና ለጤና ብርድ 5 አክሲዮኞችን፣ ለመኪናና ለቤት ብድር ደግሞ 50 አክሲዮኞችን መግዛት እንደሚያስፈልግም ነግረውናል፡፡



ምንታምር ፀጋው

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page