top of page

ጥቅምት 5፣2017 - ‘’ወደ ኦሮሚያ ክልል ስንመለስ አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ያሉ የመንግስት ተቋማት ዛሬ ያለንበትን ልንነግራቸው ብንሞክርም ሊያግዙን አልቻሉም’’ ተፈናቃዮች

ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተጠለሉት መካከል የተወሰኑት ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል መባሉ ይታወሳል።


አሁን ደግሞ የተወሰኑት እንደገና ወደ ደብረ ብርሃን እየተመለሱ መሆኑ ተሰምቷል።


ይሁንና በሰላም እጦትና በምግብ እጦት ምክንያት ከምስራቅ ወለጋ ወረዳ ብቻ 30 አባወራዎች ወደ ደብረብርሃን መመለሳቸውን ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡


‘’ወደ ኦሮሚያ ክልል ስንመለስ አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ያሉ የመንግስት ተቋማት ዛሬ ያለንበትን ልንነግራቸው ብንሞክርም ሊያግዙን አልቻሉም’’ ይላሉ፡፡


‘’አሁን ያለንበት ሁኔታ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲያግዘን እንፈልጋለን’’ም ያሉ ሲሆን ‘’በቅርብ ያሉ የመንግስት ስራ አስፈጻሚዎችም ስላለበት ሁኔታ ስንነግራቸው ሊሰሙን ፈቃደኛ አይደሉም’’ ይላሉ፡፡


አቶ ገሠሠ ረታ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የተቋቋመው ግብረ ሃይል ውስጥ የአማራ ክልሉ ዳይሬክተር ሲሆኑ፤ ‘’ተፈናቃዮቹ ዳግም ስለመፈናቀላቸው መረጃው የለንም ድጋፍ ግን እየቀረበላቸው ነው’’ ብለዋል፡፡


ተፈናቃዮቹ የኦሮሚያ ክልል ቦሳ ጎኖፋ የሚጠበቅበትን የምግብ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል።


ሆኖም በቂ እንዳልሆነና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸውም ጠይቀዋል፡፡





ማርታ በቀለ

Comments


bottom of page