ጥቅምት 4 2018 - ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች።
- sheger1021fm
- Oct 14
- 3 min read
ህንድ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የባህላዊ መድሀኒት ሀብት በሳይንስ የተደገፈ እንዲሆን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገረች።
በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የህክምና ግብዓት፣ የመድሃኒት አቅርቦት እና የህክምና እሴት ለማሳደግ ይርዳል የተባለለት ጉባኤ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በህንድ ኤምባሲ ተካሄዷል፡፡
ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከህንድ ሀገር የመጡ የህክምና ባለሞያዎች፣ የጤና ተቋማት ሃላፊዎች እና መድሃኒት አስመጪዎች ተገኝተዋል።
በመድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር፤ አፍሪካ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ቀዳሚ ተጎጂ አህጉር መሆኑን አስረድተዋል።
የሳምባ፣ ቲቢ፣ የወባ፣ ኤችአይቪ፣ የአዕምሮ ህመም፣ ካንሰር፣ ስኳር፣ ኩላሊት እና በመሰል ህመሞች አፍሪካ እንደምትሰቃይ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እነዚህን እና ሌሎች የጤና ችግሮችን ለመፍታት ከዓመታዊ በጀታቸው 15 በመቶውን ለጤናው መስክ ለመመደብ መወሰናቸውን ያስታወሱት አምባሳደሩ አባል ሀገራቱ ከዓመታዊ ጥቅል ምርታቸው (GDP) 5 በመቶ የሚሆነውን ለጤናው ዘርፍ እንደሚመድቡ ጥቁመዋል።
ከፍተኛ የሆነ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ጫና፣ ተላላፊ የልሆኑ በሽታዎች እድገት፣ የህጻናት ጤና ችግር፣የጤና ገንዘብ ድጋፍ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመሳሰሉት የአህጉሪቱ ችግሮች ሆነው ዘልቀዋል ተብሏል።
ድርቅ እና የምግብ ዋስትና፣ የሰዎች መፈናቀል፣ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች መከሰት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ የሰው ሃይል እጥረት፣ የጤና መሰረት ልማት ውስንነት እና የአዕምሮ ጤና ችግሮች ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ችግሮች እንደሆኑ አምባሳደሩ በማብራሪያቸው አስረድተዋል።
ኢትዮጵያም ዜጎቿ ተላላፊ ባልሆነ በሽታዎች ከሚቸገሩበት የአፍሪካ ሀገራት ወስጥ እንዷ እንደሆንች የሚናገሩት አምባሳደር አኒል ኩማር ህንድ በዚህ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብሮ ለመስራት እና ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ህንድ በህክምናው ዘርፍ ከፍተኛ አቅም ካላቸው ሀገራት ወስጥ አንዱ እንደሆነች ያስረዱት አምባሳደሩ ሀገራቸው በኢትዮጵያ ሆነ በአህጉሪቱ ያለው የህክምና ከፍተት ለመሙላት እየሰራች እንደሆነ አስረድተዋል።

ህንድ እጅግ የተዋጣላቸው የጤና ባለሙያዎች እንዳሏት፣ በዝቅተኛ ዋጋ ህክምና የሚገኝባት ሀገር፣ ጥራት ያለው የጤና መሰረት ልማት እና ቴክኖሎጂ፣ በአጭር ጊዜ ቪዛ የሚገኝባት እና ህክምና ለማግኘት ረዝም ቀጠሮ የሚያዝባት አገር እንዳልሆነች ለተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር በቴሌ ሜዲሲን፣ በዲጅታል ጤና ስርዓት፣ በአቅም ግንባታ እና ስልጠና፣ በጥናት እና ምርምር፣ በባህላዊ መድኃኒት እና በፖሊሲ ወይይት በመሰል ሞያዎች ሀገራቸው ኢትዮጵያን የመርዳት አቅም እንዳላት ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ የሆነ የባህላዊ ህክምና ስርዓት እንዳላቸው የተናገሩት አምባሳደር አኒል 80 በመቶ የሚሆነው ሰው በመጀምሪያ የባህላዊ ህክምና እንደሚወስድ ተናግረዋል።
እንበልና እንድ ሰው ሳል ካለበት፣ የመገጣጠሚያ ችግር ካለበት የባህላዊ መድሃኒት መውስድ ለምዷል ያሉት አምባሳደሩ ይህ ግን በሳይንስ ያልተረጋገጠ እና ያልተለየ በመሆኑ ማሰራጨት አልቻሉም ብለዋል።
እኛ እንደ አገር ይህን ለመደገፍ ዝግጁ ነን ሲሉ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር አሰረድተዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ የሆነ የጤና መብት ለመጠበቅ እያሰራ ነው ብለዋል።
መንግስት የጤናንን ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትር ዴዔታዋ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ተቋማት ይህንኑ ተግባር እየፈጸሙ ነው ብለዋል።

በዚህም በወሊድ ወቅት የሚከሰት ሞትን መሰረታዊ በሚባል ደረጃ መቀነስ እንደተቻለ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ህክምና ተቋማት ከመሄድ ይልቅ በባህላዊ መንገድ ህክምና ማድረግን እንደሚመርጡ ያረጋገጡት ወይዘሮ ሁሪያ አሊ የጤና ሚኒስቴርም ይህን ተመልክቶ መስኩን ህጋዊ አድርጎታል ብለዋል።
በዚህም ይህን ተግባር ለሚከውኑ 1200 በለሞያዎች ህጋዊ ፍቃድ እንደተሰጠ እና ከ6,000 በላይ የህክምና ዕጽዋትን መመዝገቡን አስረድተዋል።
ባህላዊ እውቀትን እና ዘመናዊን የህክምና አሰራር በማዋሃድ ኢትዮጵያ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እያሰራች ነው ተብሏል።
ይህን ላመድረግ አገሪቱ እየሰራች በላቸው ስራ ላይ የህንድ መንግስት ለመርዳት ዝግጁ ነኝ ማለቱ የሚደነቅ እንደሆነ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ለተሻለ የህክምና አገልግሎት ወደ ህንድ የሚያቀኑ ሰዎች መጠን መጨመሩን የተነገረ ሲሆን ይህም በህንድ ሀገር የሚሰጠው አገልግሎት ጥራት ብቻ ሳይሆን ዋጋዉም ተመጣጣኝ መሆኑንና እንደሚያሳየው ተጠቋሟል።
ህንድ ከአለም አምስተኛው የህክምና መዳረሻ ሀገር ስትሆን በየዓመቱ ወደ ሀገሪቱ ሄደው የሚታከሙ የሌሎች ሀገራት ዜጎች መጠን 650 ሚሊየን በላይ እንደሆነ የህንድ መንግስት ተናግሯል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments