top of page

ጥቅምት 4፣2017 - GICC በቅርቡ በኮፕሬቲቪ ፍሬም ወርከር አግሪመንት ዙሪያ ጉባኤ ያደርጋል ተባለ

መቀመጫቸውን በአሜሪካ እና በተለያዩ አለማት አድርገው ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በሚመለከት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ኢትዮጵያ የምታደርገውን ሙግት የሚደግፉ ባለሙያዎች ተቋማትን በአንድ ያሰባሰበው (GICC) በቅርቡ በCFA ዙሪያ ጉባኤ ያደርጋል ተባለ፡፡



የአባይ ውሃ አጠቃቀምን በሚመለከት በተፈረመው (CFA) ኮፕሬቲቪ ፍሬም ወርከር አግሪመንት የወደፊት ጉዞ ዙሪያ ጭምር ለመምከር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለሸገር ራዲዮ የነገሩት የGICC ወይም ግራንድ ኢንተርናሽናል ኮላቦሬቲቭ ኮንሰርቲየም አስተባባሪው አባተ ታደሰ(ዶ/ር) ናቸው፡፡



የኔነህ ሲሳይ

Comments


bottom of page