top of page

ጥቅምት 4፣2017 - የኢትዮጵያን ዓመታዊ ጥቅል ምርት ለማስላት የሚጠቅም መረጃ የሚሰበሰብበት ጥናት መጀመሩን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ

የኢትዮጵያን ዓመታዊ ጥቅል ምርት ለማስላት የሚጠቅም መረጃ የሚሰበሰብበት ጥናት መጀመሩን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተናገረ፡፡


በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየከበደ የመጣውን የኑሮ ጫና መቋቋም የሚሳናቸው፤ በጦርነትና በተፈትሮ አደጋ ከቋሚ ገቢና ስራቸው የሚፈናቀሉ፤ በዚህም የተነሳ ወጪያቸውን መሸፈን እያቃታቸው የሰዎችን እጅ ለማየት የሚገደዱ ሰዎች በርካታ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ይሁንና አሉ ከማለት ባለፈ የትና በምን ሁኔታ ውስጥ ናቸው፤ ከዚህ እንዲወጡ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ለማወቅ መለየት በማስፈለጉ ወደጥናት እንደገባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነግሮናል፡፡


የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳፊ ገመዲ የኢትዮጵያ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት በያዝነው ዓመት መጀመሩንና ጥናቱ በኢትዮጵያ ያለው እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል ገቢ ያገኛል፡፡


ከሚያገኘውስ ምን ያህሉን ለምግብ፣ለቤት ኪራይና ለሌላውም ያወጣል የሚለው እንዲሁም ከህዝቡ ምን ያህሉ በሃገር ውስጥና ወደ ውጭ ይፍልሳል፣የጤናና ትምህርት ተደራሽነቱስ ምን ያህል ነው? የሚለውም ጭምር እንደሚጠና ጠቁመዋል፡፡


ጥናቱን ማድረግ ያስፈለገው ማህበረሰቡ ያለበትን የኑሮ ደረጃ በመመልከት ለማሻሻል በመንግስት ለሚሰናዱ የስራ እድል ፈጠራ ፕሮግራሞች ግብአት ለማሰባሰብ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሳፊ ጥናቱ ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያካልል ነውም ብለዋል፡፡


የጥናቱ አካሄድ ሳምፕል በመውሰድ የሚከወን ነው ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/ymdpey4s


ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page