top of page

ጥቅምት 4፣2017 - ከ45 የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 250 ወጣቶች በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡

ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ስለ አህጉሪቱ የ #ሥርዓተ_ምግብ ለመነጋገር ነው፡፡


ተፈጥሮ ላይ መሰረቱን ያደረገ የምግብ ልዓላዊነት ላይ ለመምከር ወጣቶቹ ተሰባስበዋል፡፡


ፕሮግራሙን ያሰናዳው ደግሞ በምግብ ሉአላዊነት ላይ የሚሰራው Alliance for food sovereignty in Africa (AFSA) የተባለ ተቋም ነው፡፡


በምግብ እጦት፣ በተመጣነ ምግብ ችግር ውስጥ ያለችው አፍሪካ ይህንን ችግር በሀገር በቀል እውቀት ታግዛ ምርት እንድታመርት፣ የሌላው አለም ማዳበሪያ፣ መድሃኒትም ሆነ #ምርጥ_ዘር ጥገኛ እንዳትሆን መላ ማበጀት የአዲስ አበባ የAFSA ጉባኤ አጀንዳ ነው፡፡

የገበሬ ሀገሯ ኢትዮጵያ ግብርናዋ እንደ እድሜውና እንደሚያስተዳድረው ህዝብ ብዛት ሊያድግ አልቻለም፡፡


ግብርናው ከበሬ ትከሻ፣ ከሞፈር እና ቀንበር አልተላቀቀም፡፡


የአብዛኛው የአፍሪካ ሀገር የግብርና ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ይህን የአፍሪካ ታሪክ እንዲቀየረ ነው ኢትዮጵያ ስለ #ግብርና አብዝታ የምትናገረው እና እንስራ የምትለው ብለዋል፡፡


የአትዮጵያም ሆነ የአህጉረ አፍሪካ ግብርና ህዝቡን አጥግቦ መመገብ አልቻለም፡፡

ለዚህም በአብዛኛው የሚታየው መፍትሄ #ማዳበሪያ መጠቀምን፣ የተሻሻሉ ብዙ ምርት የሚሰጡ ዘፎች ማብዛት የመሳሰሉ ናቸው፡፡


የወጣቶቹን ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ያለው AFSA በበኩሉ ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ ሀገር በቀል ዘር የመሳሰሉት ናቸው የአፍሪካ የምግብ ችግር ሊፈቱ የሚገባው ይላል፡፡


የአፍሪካ የምግብ ሉአላዊነት ላይ 250 ወጣቶች ከ45 የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባ ላይ ያገኘነው ከ2,000 በላይ ሌሎች ሰዎች ደግሞ በበይነ መረብ መላ አማካይነት እያሳተፈ ሶስት ቀናት የሚመክረው ጉባኤ በሀገር በቀል እውቀት ዘዴ እንዴት የአህጉሪቱ ህዝብ ጠግቦ ይብላ የሚለው ላይ ሀሳብ ያዋጣል ተብሏል፡፡



ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page