የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በእሳት አደጋ ሰራተኞቼ ላይ የስም ማጥፈት ዘመቻ በከፈቱ አካላት ላይ ክስ መስርቻለሁ አለ፡፡
በመርካቶ #ሸማ_ተራ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ከመጥፋት ይልቅ በገንዘብ ሲደራደሩ፣ ሲቀበሉ ነበር እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር እንደነበር ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ በወቅቱ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ሲረባረቡ በነበሩ ሰራተኞቻችን ላይ ያለምንም ማስረጃ ስማቸውን ባጠፉትና ተቋሙንም የማጠልሸት ዘመቻ ባካሄዱ የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶችና ግለሰቦች ላይ #ክስ መስርተናል ሲሉ ለሸገር 102.1 ሬዲዮ ተናግረዋል።
አቶ ንጋቱ #የእሳት_አደጋ ሰራተኞች ሙያቸውን የሚከውኑት እስከ ህይወት መስዋእትነት ድረስ ነው ብለዋል።
ኮሚሽኑ ለፖሊስ ክስ ያቀረበበት የስም ማጥፋት ወንጀል ውጤት ከፖሊስ ምርመራ በኋላ ይፋ እንደሚደረግም አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
コメント