top of page

ጥቅምት 29፣2017 - የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት ጉዳይ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አደፍርሷል፡፡


ጉዳዩም እየረገበ ሳይሆን እየተካረረ የሄደ ይመስላል፡፡


ይህም ቀድሞንም ለኢትዮጵያ ልማት እንቅፋት መሆኗ ለሚነገርላት ለግብፅ እድል ሰጥቷታል የሚሉ የተለያዩ ማሳያዎችን ያነሳሉ፡፡


በመሆኑም ኢትዮጵያ አሁን ካኮረፈችው ሶማሊያ ምን አጣለሁ? ከሶማሌላንድስ የማገኘው ጥቅም ምን ይሆናል? የሚለውን ከቋሚ ብሔራዊ ጥቅም አንፃር በመገምገም እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባት ሸገር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተመራማሪ መክረዋል፡፡




ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page