የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አያያዝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሊገመገም ነው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ #ሰብአዊ_መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ በአራተኛ ዙር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ መድረክ ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡
የግምገማው ቡድኑ ስብሰባውን ህዳር 3 በጄኔቭ እንደሚያደርግና ሒደቱም በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል ተብሏል፡፡
ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር 14 ሀገሮች ይገመገማሉ፡፡
የግምገማው ቡድኑ 47 የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ያቀፈ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራትን በግምገማው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
የአገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማው የሚደረገው ሀገራዊ #ሪፖርት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡
ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች እና ቡድኖች ሪፖርቶች ሀገራት በተቀበሉት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ዙሪያ የሚያከናውኑ አካላት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ሪፖርት ውስጥ የተካተቱ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነው፡፡
ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን ጨምሮ ሌሎች አካላት ባቀረቡት መረጃዎች ላይ መሰረት በማድረግ ሪፖርቱ ይቀርባል፡፡
Comments