top of page

ጥቅምት 28፣ 2017 - በምስራቅ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተከሰቱ ግጭቶች ቤት ንብረት ለወደመባቸው እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚደረገው እርዳታ ዝቅተኛ ነው ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በተለያ ወረዳዎች በተከሰቱ ግጭቶች ቤት ንብረት ለወደመባቸው እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚደረገው እርዳታ ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡


ለተጎጂዎቹ አቅም በፈቀደ መልኩ ድጋፍ እየተደረገላቸው ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ሰምተናል፡፡


በዚህም የረድኤት ድርጅቶች ሆኑ ሌሎች አካላት ድጋፍ ሊያደርጉልን ይገባል ሲል ዞኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡


ተጎጂዎቹ፣ ከምስራቅ ወለጋ ከተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው እዚያው ዞን ውስጥ በሚገኙ የመጠለያ ጣቢያዎች እና በየግለሰብ ቤቶች ተጠግተው የሚገኙ እንደሆኑም ሰምተናል፡፡


በመጠለያ ጣቢያ ያሉት ሰዎች ቁጥር ቀድሞ ከነበረበት አሁን ላይ ቀንሷልም ተብሏል፡፡


ወደ ዞኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ሆኑ፤ ሌሎች ረጂ ድርጅቶች እርዳታ በማድረሱ ክፍተት እንዳለም ተነግሯል፡፡


ረጂ ድርጅቶች ወደ ዞኑ ሄደው እንዳያግዙ በአካባቢው የተከሰተው የጸጥታ ችግር ስጋት አሳድሮባቸው ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡


በዚህ ጉዳይ ምላሹን ለሸገር ራዲዮ የነገረው የምስራቅ ለወጋ ዞን፤ ለረጂ ድርጅቶች የሚያሰጋ አይደለም፤ አቅም ያለው ድርጅትም ይሁን ሌላ አካል ተጎጂዎቹን በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ ማገዝ ይችላል ብሏል፡፡


‘’ጅረት ለእርቅ እና ለሰላም’’ የተሰኘ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፤ በምስራቅ ወለጋ አካባቢ ያሉት የግጭት ተጎጂዎችን የቁስ ድጋፍ እና የስነ-ልቦና ስልጠና እየሰኋቸው ነው ብሏል፡፡


ለመሆኑ በዞኑ የሚገኙ ተጎጂዎች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ የአካባቢውስ የሰላም ሁኔታ እርዳታ ለማድረስ አስቻይ ነው ወይ? ስንል ጠይቀናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ


ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page