top of page

ጥቅምት 28፣2016 - የብዝሃሕይወትና የሥነ ምህዳርን መመናመን መቀነስ አልተቻለም ተባለ

ብዝሃሕይወትና ስነ ምህዳር፤ ለሚበላው፣ ለሚጠጣውም፣ ለሚለበሰውም ከፍተኛ ድርሻ ቢኖረውም በተለያዩ ምክንያቶች እየተሸረሸረ ነው ተብሏል፡፡


ከዚህበፊት ጥፋቱን ለመቀነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ውጥኖች ቢወጠኑም ሀገራት ግን የገቡትን ቃል 25 በመቶውን ያህል እንኳን ማሳካት እንዳልቻሉ የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማሪዮ ተናግረዋል፡፡

የብዝሃሕይወት መመናመን የአየር ንብረት ለውጥ የአየር ብክለት፣ ለጎርፍ እና ለተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡


በዚህዙሪያ በስነ ምህዳርና በብዝሃ ሕይወት ላይ ያለውን ግንዛቤ ለማሻሻል አህጉር አቀፍ የሁለት ቀንየባለሞያዎች ስልጠና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡


ስልጠናውለአፍሪካ አገራት ፖሊሲ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች ይበጃል ተብሏል፡፡ያሬድ እንዳሻውየሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Kommentarer


bottom of page