ጥቅምት 27፣ 2017 - ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት መሆን የሚያስችላቸው ውጤት አግኝተዋል ተባለ
- sheger1021fm
- Nov 6, 2024
- 1 min read
ሪፖብሊካዊው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት እጩ ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት መሆን የሚያስችላቸው ውጤት አግኝተዋል ተባለ፡፡
ትራምፕ 279 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
በምርጫው ለማሸነፍ የሚያስችል 270 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ብቻ ነበር፡፡
ይሁንና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የቅድሚያ ውጤቱ አሳይቷል፡፡
የዴሞክራቶቹ ፕሬዘዳንታዊ እጩ ካምላ ሐሪስ ያገኙ ደግሞ 223 ኢሌክቶራል ኮሌጅ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሪፖብሊካውያኑ የአሜሪካን የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አብላጫነት መያዛቸው እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
Comentarios