ጥቅምት 27፣ 2017 - ዶናልድ ትራምፕም በዌስት ፓልም ቢች ወደተዘጋጀው የድል ፈንጠዝያ ዝግጅት መድረሳቸው ታውቋል
- sheger1021fm
- Nov 6, 2024
- 1 min read
ዶናልድ ትራምፕም በዌስት ፓልም ቢች ወደተዘጋጀው የድል ፈንጠዝያ ዝግጅት መድረሳቸው ታውቋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ድል ወደ ሪፖብሊካዊው እጩ #ዶናልድ_ትራምፕ እያጋደለ ነው፡፡
የቅድሚያ ውጤቶቹም ይሔንኑ ያሳያሉ፡፡
ትራምፕ፣ ደጋፊዎቻቸውም በፍሎሪዳ ዌስት ፓልም ቢች ከወዲሁ ታላቅ ፈንጠዝያ ማሰናዳታቸው የድሉ አመላካች እንደሆነ ቢቢሲ ጽፏል፡፡
በሥነ - ሥርዓቱም ላይ ''ባለ ታላቅ ድል ሆነናል'' ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የምርጫው የፍልሚያ ሜዳዎች በሚሰኙ ግዛቶች ስዊንግ ስቴትስ የትራምፕ ደጋፊዎች ፈንጠዝያ ላይ ናቸው፡፡

የዴሞክራቷ እጩ #ካምላ_ሐሪስ ደጋፊዎች በሆዋርድ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅተውት ከነበረ መሰል ዝግጅት ቀስ በቀስ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡
የሀሪስ ደጋፊዎች በእጅጉ ማዘን እና መከፋታቸው ከፊታቸው ይነበባል ተብሏል፡፡
በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት)ም ሪፖብሊካውያን አብላጫነቱን ማግኘታቸው እንደማይቀር ተነግሯል፡፡
ትራምፕ አገኙት የተባለው ውጤት ከወዲሁ እንደ ታላቅ ፖለቲካዊ ስኬት እየተቆጠረላቸው ነው፡፡
የትራምፕ #የምርጫ_ውጤት ከ8 ዓመታት በፊት የነበረውን ድላቸውን አስታዋሽ ሆኗል፡፡
#በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈው፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
Comments