top of page

ጥቅምት 27፣ 2017 - በአካል ጉዳተኞችና በአረጋውያን መብቶች ዙሪያ፣ አሳሳቢ ጉዳዮች መታየታቸውን ኢሰመኮ ይፋ አደረገ

በዘንድሮው የበጀት ዓመት በአካል ጉዳተኞችና በአረጋውያን መብቶች ዙሪያ፣ አሳሳቢ ጉዳዮች መታየታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ይፋ አደረገ፡፡


በትጥቅ ግጭቶች ዐውድ ውስጥ በሚፈጠሩ፣ #የሰብአዊ_መብት_ጥሰቶች አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ንብረታቸው ተዘርፏል፡፡


በሴት የአዕምሮ ህሙማን ላይ ያተኮረ ፆታዊ ጥቃት መታየቱን የጠቆመው ኢሰመኮ፣ በሰዓት እላፊና የእንቅስቃሴ ገደቦች፣ በአነስተኛና በጥቃቅን ንግድ ስራ ዘርፍ የሚተዳደሩ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ለችግር መጋለጣቸውን በሪፖርቱ አካቷል፡፡


አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች በሚካሄዱ የልማት ስራዎች፣ #አካል_ጉዳተኞች አረጋውያን በችግር ላይ መውደቃቸውን ለዚህም ምክንያት ምትክ ቦታዎች ሳይሰጣቸው እንዲነሱ በመደረጉ መሆኑን ጠቅሷል፡፡


አካል ጉዳተኞች የገጠሟቸውን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዋና ሀላፊነቱ የመንግስት መሆኑን ጠቅሶ ሃገራዊና አለም አቀፋ የሰብአዊ ድርጅቶች እንዲያግዙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡


እሸቴ አሰፋ

Comments


bottom of page