top of page

ጥቅምት 27፣2016 - የመንግስት ግዢ ሙሉ ለሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ ግዢ ሥርዓት መምጣቱ ሌብነትን እንዲቀንስ ያደርጋል ብለዋል

በ2016 የበጀት ዓመት 164 የፌደራል ተቋማት የመንግስት የኤሌክትኖኒክስ ግዢ ሥርዓትን እየተገበሩ ነው ተባለ።


ቀሪ 5 የሚሆኑ ተቋማት በትግራይ እና አማራ ክልል ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት እስካሁን የኤሌክትሮኒክስ ግዢ ሥርዓቱን አልተገበሩም ተብሏል፡፡


በሚቀጥሉት ወራት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀጂ ኢብሳ እንዳሉት መንግስት እንደ ፌዴራል በተያዘው ዓመት የፌደራል መስሪያ ቤቶች ግዢን ሙሉ ለሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ የግዢ ሥርዓት አስገብቷል ብለዋል።


በ2016 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 2,802 ጨረታዎች በዚህ ስርዓት መውጣታቸውን ተናግረዋል።


የመንግስት ግዢ ሙሉ ለሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ ግዢ ሥርዓት መምጣቱ ሌብነትን እንዲቀንስ ያደርጋል ብለዋል።

በተለይ በጨረታ ወቅት ይመዘበር የነበረ የመንግስት ሀብት ከመዳኑም ባለፈ አንዳንድ ተቋማት ከነጋዴው ጋር በሽርክና ይሰሩ እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።


አሁን ላይ አስራ አምስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጨረታዎችን ለመሳተፍ በኤሌክትሮኒክ ግዢ ሥርዓቱ ተመዝግበዋል ተብሏል።


የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለስልጣን እንዳለው በ2015 በጀት ዓመት በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዢ 56.8 ቢልዮን ብር ግዢ መፈፀሙን ተነግሯል።


የተለያዩ የውጪ ሀገር ተቋማት በኤሌክትሮኒክ ግዢው ላይ ለመሳተፍ እየጠየቁ መሆኑን ሰምተናል።


ከፌደራል ተቋማት ውጪ በአዲስ አበባ እና በሲዳማ ክልል የመንግስት ኤሌክትሪክ ግዢ ስርዓትን እየሞከሩ ነው ተብሏል።


ከ164 የፌዴራል ተቋማት ውስጥ 161 የሚሆኑት የግዢ እቅድ አስገብተዋል ሲሉ አቶ ሀጂ ኢብሳ ተናግረዋል፡፡


በረከት አካሉየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

コメント


bottom of page