top of page

ጥቅምት 26፣2017 - የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዮናስ አሽኔ(ዶ/ር) በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ገለልተኛነት ላይ ያላቸውን ስጋት ተናግረዋል

አላግባብ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮችን በምክክር ለመፍታት እና የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ያግዛል ተብሎ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለልተኝነት ላይ በተለይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ታጣቂ ቡድኖች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል፡፡


ኮሚሽኑ በበኩሉ ገለልተኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡


በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ምሁራንም በተገኙት በጉዳዩ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡


አላግባብ ያሉ ለዘመናት የቁርሾ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች በምክክር ለመፍታት #የሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን መቋቋም ይታወሳል፡፡


በዚህ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ጥርጣሬ አለ በኮሚሽኑ ምስረታ ሂደት ላይም ቅሬታ አለን ያሉ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የታጠቁ ቡድኖች በምክክር ሂደቱ ላይ ተሳታፊ አይደለንም ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆኑ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም የመሠረቱት እና ፖለቲከኛውን #መስፍን_ወልደ_ማሪያምን ለመዘከር በተሰናዳው መድረክ ላይ ይህ ጉዳይ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡


የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዮናስ አሽኔ(ዶ/ር) በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ገለልተኛነት ላይ ያላቸውን #ስጋት ተናግረዋል፡፡


እርሳቸው እንደሚሉት ባለፉት ዓመታትም ቢሆን በኢትዮጵያ ነፃ የሆነ ተቋም መገንባት አልቻልንም ይላሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ



ማርታ በቀለ

Comentários


bottom of page