top of page

ጥቅምት 26፣2017 - ከኢነርጅ ሽያጭ፣ ከደንበኞች አገልግሎት ክፍያ እና ከሌላ ሌላውም 11.15 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።

ከኢነርጅ ሽያጭ፣ ከደንበኞች አገልግሎት ክፍያ እና ከሌላ ሌላውም 11.15 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።


አገልግሎቱ ይህንን የተናገረው የሩብ ዓመቱን አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።


ተቋሙ በ2017 በበጀት ዓመት ሶስት ወራት፣ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች 11.55 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 11.15 ቢሊዮን ብር #ገቢ እንዳደረገ ጠቅሶ የእቅዱን 97 በመቶ አሳክቻለሁ ብሏል።


በዚህም የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 41.4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተመልክቷል።


በተጨማሪም 31 አዳዲስ #የገጠር_መንደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 26 የሚሆኑ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።


ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ በከወነው ስራ የእቅዱን 83 በመቶ ማሳካቱን አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_አገልግሎት ለብልሹ አሰራር መጋለጡን ያልሸሸጉት አቶ መላኩ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት 20 የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ስራ ማሰናበት ድረስ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።


ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቃቸው፣ የሀይል መቆራረጥ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መኖሩ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት አጋጥመዋል ከተባሉት ችግሮች መካከል ናቸው።


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page