top of page

ጥቅምት 26፣2017 - ''አዲስ አበባ ሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል'' ለ300 ሰዎች ነፃ ህክምና እየሰጠ ነው

''አዲስ አበባ ሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል'' ለ300 ሰዎች ነፃ ህክምና እየሰጠ ነው።


ሆስፒታሉ ነፃ ህክምና ለአምስት ተከታታይ ቀናት እየሰጠ ያለው፤ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ነው።


በዚህም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የሚገኙ ከፍለው ለመታከም እጅ ላጠራቸው ከህፃን እስከ አረጋዊ ያሉ ሰዎች የእድሉ ተጠቃሚ መሆናቸው ተነግሯል።


በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ እና በፅዳት ሰራተኝነት የሚሰሩ እንዲሁም ከፍለው ለመታከም ላልቻሉ ሰዎች በሚደረግ ጥሪ መሰረት እየታከሙ መሆኑን ሰምተናል።


ህክምናውም ከአጠቃላይ ምርመራ እስከ መድሃኒት መስጠት ድረስ እንደሚያካትት ተነግሯል ።


ህክምናውን የሚሰጡት ከቻይና ሀገር የመጡ በጎ ፍቃደኛ ሀኪሞች እና የሆስፒታሉ ሀኪሞች መሆናቸውን ሲነገር ሰምተናል።


ሆስፒታሉ ይህን መሰል ነፃ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የዘንድሮውን ጨምሮ ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋንግ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ ህክምናው ለሁሉም እንዲደርስ ከቻይና ሀገር ከፍተኛ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን ሀኪሞች ወደ ኢትዮጵያ እያመጡ በነፃ ህክምና እንዲሰጥ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።


ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ሀኪሞች ወደ ቻይና ሀገር ሄደው እንዲሰለጥኑ እና ህዝባቸውን በበለጠ እንዲያገለግሉ እናደርጋልን ብለው ቃል ገብተዋል።


ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ሲልክ ሮድ ሆስፒታል ከሁለት ቋማት ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል።


አንደኛው ስምምነት ሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል በዲቦራ ፉውንዴሽን ውስጥ የእድገት እና የአዕምሮ ውስንነት ላለባቸው ሰዎች የምርመራ ማዕከል መገንባት ነው።


ሌላኛው ስመምነት ደግሞ ‘’ሀኒያ’’ ከሚባል የቻይና የአካል ድጋፍ አምራች ኩባንያ ጋር የተደረገ ስምምነት ነው።


ይህን ስመምነት የተፈራረሙት ደግሞ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ ተቋም እና የቻይናው የካል ድጋፍ አምራች ሀኒያ ናቸው።


በስመምነቱ መሰረት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደ ዊልቸር የመሳሰሉ የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች በኢትዮጵያ ለማምረት ያስችላል ተብሏል።


በኢትዮጵያ የተለያየ የአካል ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ብዛት ከ10 ሚሊዮን እንደሚበልጥ የጤና ሚኒስትር ድኤታው ደረጀ ድጉማ(ዶ/ር) ሲናገሩ ሰምተናል።


ንጋቱ ሙሉ

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page