top of page

ጥቅምት 26፣2017 - በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ

  • sheger1021fm
  • Nov 5, 2024
  • 1 min read

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ፡፡


አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ አቀባበል ተደረጎለታል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን A350-1000 "Ethiopia land of origins" የተሰኘ #የመንገደኞች_አውሮፕላን ከኤር ባስ ኩባንያ በትናንተናው ዕለት መረከቡ ይታወሳል፡፡

አውሮፕላኑን ፈረንሳይ ሄደው ተረክበዉ ያመጡት የአየር ኃይል ዋና አዛዥና ኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተና ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሥፍን ጣሰው ናቸው።


አቶ መሥፍን ባደረጉት ንግግር የዚህ አውሮፕላን መገዛት ለኢትዮጰያ #አቬሽን ታሪክ ከፍተኛ ኩራት ይሰጣል ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ መናገራቸው ይታወቃል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page