top of page

ጥቅምት 25፣2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ

  • sheger1021fm
  • Nov 4, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ።


ገደቡ የተነሳው ለጊዜው እንደሆነና ይህም ከባንክ ወደ #ቴሌ_ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ አንደሆነ ሸገር 102.1 ራዲዮ ከምንጮቹ ሰምቷል።


የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል፡፡


መንግስት ወይም #የኢትዮዽያ_ኢንቨስትመንት_ሆልዲንግ ግዙፋን ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።


ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።


የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።


በተጨማሪም የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።


የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ ነው።


ተህቦ ንጉሴ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page