top of page

ጥቅምት 25፣2017 - በ2017 የትምህርት ዘመን ለረመዲያል ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን ለረመዲያል ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡


በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በረመዲያል ለመማር የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ፤ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እነዚህ አድራሻዎችን በመጠቀም መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡


በዌብሳይት፤ https://placement.ethernet.edu.et ወይም ቤቴሌግራም፤ https://t.me/moestudentbot


በቀጣይም ለመንግስት ተጠሪ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በሚያሳውቁት የጥሪ ቀን መሰረት ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያከናውኑም ጠቁሟል፡፡


የዩኒቨርሲቲ ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም ሲልም ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 94.6 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አላስመዘገቡም መባሉ ይታወሳል፡፡

Comments


bottom of page